ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከቻይናው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር
የምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከቻይናው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር

ከ 9 ሰአት በፊት

ወደ ሌሎች ሀገራት በመጓዝ የስራ ጉብኝት ሲያደርጉ እምብዛም የማይስተዋሉት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ቤጂንግ አቅንተዋል።

በጉብኝታቸውም ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር ተነጋግረዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዘመናዊቷን ቻይና ለመገንባት በተደረገው ትግል የሞቱ ሰዎች በሚዘከሩበት ቲያናማን አደባባይ ላይ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1989 ታይናማን አደባባይ ፖለቲካዊ ነጻነትን በሚጠይቁ ተቃዋሚዎች በማስተናገድ ትኩረትን ስቦ ነበር።

ተቃውሞ በቻይና ባለስልጣናት በተወሰደ እርምጃ ቆሟል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቻይና የአለምን ስርዓት ለመቀየር ታደርጋለች ላሉት አስተዋጾ አድናቆታቸውን ቸረዋል።

የኤርትራ መንግስት በዓለም ላይ ካሉ ጫቋኝ መንግስታት አንዱ ነው።

በዓለም አቀፍ አካባቢያዊ ፖለቲካ ለቻይና ጠቃሚ የሆነቸው ኤርትራ ባልተገባ የሰብአዊ መብት አያያዝ በተደጋጋሚ በምዕራባውያን ሀገራት ትተቻለች።

ቻይና በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ወታደራዊ ሰፈር የገነባች ሲሆን በብዙ ፈተና ውስጥ ባለው የአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ተጽዕኖዋን ለማሳደግ ጥረቷን ቀጥላለች።