
ምንሊክ ሳልሳዊ ፡ ሕግ አውጪውም፣ ሕግ አስፈጻሚውም፣ ሕግ ተርጓሚውም ያላከበረው ፣ ለሕዝብ ያልበጀው፣ በኢሕአዴግ የፖለቲካ ፕሮግራም የተቀረጸው (ሕገ አራዊት) ሕገመንግስትን ከማሻሻል በፊት ሕግና ስርዐት ያለው መንግስት ይኑር ። ሕገመንግስት ማሻሻል የሁላችንም የአስርት አመታት ጥያቄ ቢሆንም የሃገርን ሰላምና የዜጎችን ደሕንነት መጠበቅ ያልቻለ መንግስት ባሌለበት እንዴት ሕገ መንግስት ይሻሻል ይባላል ? ቅድሚያ መንግስት ይኑር ! በኢመደበኛ ስም አዘናግቶ ብልጽግና የፈለገውን አምጥቶ ሊጭንብን ልንፈቅድለት አይገባም።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኮሚሽን ለሚዲያ ፍጆታ መስርቶ የሚያፈርሰው የአብይ አስተዳደር የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን በጀት እንዳገደው ሰምተናል። እነ ኢዜማ ተስፋ የጣሉበት ይህ ኮሚሽን ወዴት እያመራ ነው ውይይት እያሰናዳሁ ነው ብሎ ሊወድቅ እየተንገዳገደ መሆኑ ሲሰማ ያው እጣው ካሁን ቀደም እንደተባለው እንደ እርቀ ሰላም ኮሚሽን እና የወሰን ማካለል ኮሚሽን የመፍረስ አደጋው ከሕገ መንግስት አሻሻይ አዳዲስ ኮሚቴዎች መቋቋም ጋር ተከትሎ መሆኑ ስንሰማ ሃገሪቷ መንግስት አልባ መሆኗን ምስክር ነው።
የሕገ መንግስት መሻሻልን የሚመለክተው አካል የሕገ መንግስት አርቃቂ ጉባዬ ሆኖ ሳለ አብይ አሕመድ ፖሊሲ ይነድፉልኛል ብሎ ያሰባሰባቸው የፖለቲካ አሽከሮቹ ስለሕገ መንግስት መሻሻል ሲነግሩን አግራሞትን ፈጥረዋል። የሕገ መንግሥት መሻሻል የዘመናት ጥያቄአችን፣ ሕልማችንም ነበር። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ለአኔ የቅንጦት ጥያቄ ነው። ኢመደበኛ የሕገመንግስት ማሻሻያ : ሕጉ ምንድነው የሚለው ? ማነውስ እንዲያሻሽለው የሚፈቀድለት ? የሕገመንግስት ጉባዬውስ ? ብዙ ጥያቄዎች የሚያስነሳ ኢመደበኛ የሕገ መንግስት ማሻሻያ ነው ። ሕገወጥነትን በጋራ ልንታገለው ይገባል። #MinilikSalsawi
