
የኢትዮጵያ ሕዝብ በመንግስት የሚደረጉ የቤተመንግስት ግንባታዎች ላይ ጥያቄዎችን እያነሳ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ850 ቢሊዮን ብር ቤተመንግስት እያስገነቡ ሲሆን የኦሮሚያ ክልልላዊ መንግስት ደግሞ ተረኝነቱን ተገን አድርጎ በርካቶችን በማፈናቀል በ500 ቢሊዮን ብር ቤተመንግስት ሊገነባ መነሳቱ ጥያቄ አስነስቷል። ይህ ጥያቄ ያስነሳው ከሃገሪቱ ኢኮኖሚ እና በርካታ የሕዝብ ንብረቶች በወደሙባትና ሕዝብ እየተፈናቀለ በረሃብ በሚቸገርበት አገር የውስጥ ችግሮች ሳይፈቱ በቅንጦት ግንባታዎች ላይ መተኮሩ መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ አነጋጋሪ ሆኗል።
በዛሬው እለት የተሰማው ዜና በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኝ ከስድስት ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ፤ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቤተ መንግሥት ሊገነባ ነው ተብሏል። ሕዝብ በ850 ቢሊዮን ብሩ ላይ ጥያቄ እያነሳ ሌላ በ500 ቢሊዮን ይገነባል መባሉ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ሊፈጥረው የሚችለውን ችግር አለማጤን መሆኑ ተነግሯል።
በጠ/ሚ አይዞህ ባይነት በኦሮሞ ብልጽግና መሪ ካድሬዎች የሚዘወረው፣ ጋጠ ወጥነት፣ የተደራጀ ምዝበራና ሙስና እና መብት ረገጣ እንታገል !
2 ቢሊዮን $ ከአለም ባንክ ብድር ትለምናለህ፣ የተፈናቀሉ ሚሊዮኖች በቂ ድጋፍ ባላገኙበት፣ እስርቱ ሺዎችም አፈናቅለህ ለልመና ዳርገህ፣ በየመጠለያው ተርበው ተጠምተው የ 10 ቢሊዮን + ቤተ መንግስት ትገነባለህ፣ የሰብእና የህሊና እውርነት! መንግሥት ላይ ማእቀብ መጣል ህዝብን/አገርን መጉዳት አይደለም። መንግሥት የአገሪቱን ሃብት ለጦርነት፣ለድግሥ እና ላልተጠና መዝናኛ ግንባታ ይጠቀማል። ጥቁር ገበያ ውስጥ ገብቷል፤ባለሥልጣናቱ እየዘረፉ ነው።ይህንን ጥፋት እንዲያቆም ማስገደድ ነው::
ተጠያቂነትና ግልጽነት የሌላቸው የጠ/ሚንስትሩ የቤተ መንግስት ግንባታና፣ የቅንጦት ፕሮጄከቶች 850 ቢሊዮን ብር (15 ቢሊዮን $) እንዲሰረዝ፣ የሚሊዮኖች ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎት እንዲሟላ መሞገት፣ መታገል ::
የውጭ ብድሮችና ኢኮኖሚያዊ እርዳታዎች ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ በውጭ የምንገኝ ሀገር ወዳዶች ሁሉ መታገል፣ መሟገት ወቅቱ የሚጠይቀው ሰላማዊ የትግል ስልት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶች መጠለያ፣ ምግብ፣ ንጹህ ወሃ፣ መብራት፣ ለመሰረት ልማት የብድሮችና የእርዳታዎች ቅድመ ሁኔታዎች እንዲደረጉ መታገል፣ መሟገት አለብን።
በጠ/ሚ አይዞህ ባይነት በኦሮሞ ብልጽግና መሪ ካድሬዎች የሚዘወረው፣ኢ-ሀገ መንግስታዊነት፣ ጋጠ ወጥነት፣የተደራጀ ምዝበራና ሙስና፣ ሰፊ አፈና: ሰብአዊ መብቶች ረገጣ፣ነቀላና ፍንቀላ በበቂ ተሰንዶ፣ ለመንግስታት ለአለም አቀፍ ተቋማት ማቅረብ: …… የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ሰብአዊ መብቶች ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበሩ እንዲረጋገጡ ተደራጅተን፣ ተናበን መሞገት: መታገል አለብን።
