
ከ 3 ሰአት በፊት
ኬንያ የአገልግሎት ጊዜው ያለፈበት ስኳር ለገበያ መቅረቡን ተከትሎ 27 ባለስልጣናትን ከስራ አገደች።
የኬንያ የጥራትና ደረጃ ተቆጣጣሪ 1 ሺህ ቶን የሚሆን የአገልግሎት ጊዜው ያለፈበት ስኳር ወደ ገበያ መውጣቱን ጠቁሞ ይህንን ባደረጉ ባለስልጣናትም እርምጃ ተወስዷል ብሏል።
የህዝብ አገልግሎት ኃላፊው ፊሊክስ ኮስኬይ በሰጡት መግለጫ በአውሮፓውያኑ 2018 ወደ አገር ውስጥ የገባ 20 ሺህ ከረጢት ስኳር በተቆጣጣሪው አካል ከጥቅም ውጭ ነው በሚል ከገበያ ውጭ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፎ ነበር ብለዋል።
ነገር ግን ይህ ወደ ገበያ እንዳይቀርብ ክልከላ የተጣለበት ስኳር ያለ አግባባብ ለገበያ እንዲውልም መደረጉን ገልጸዋል።
የኬንያ የጥራትና ቁጥጥር ቢሮ ስኳሩን ለሰው ልጅ ፍጆታ የማይመጥን ነው በሚል ውሳኔ በወቅቱ አስተላልፎ ነበር።
ይህንንም ስኳር ወደ ኢንዱስትሪዎች ወደ ኢታኖል ንጥረ ነገር እንዲቀይሩት በማድረግ እንዲወገድም ብሎ ነበር።
- ሩሲያ የዩክሬንን መዲና ለዘጠነኛ ጊዜ በሚሳኤል አጠቃችከ 5 ሰአት በፊት
- የአሜሪካዋ ሞንታና ግዛት ቲክቶክን ግለሰቦች እንዳይጠቀሙ ልታገድ ነውከ 4 ሰአት በፊት
- ልዑል ሃሪ እና ሜጋን ‘ፓፓራዚዎች’ ኒው ዮርክ ውስጥ “በመኪና አሳደዱን” አሉከ 4 ሰአት በፊት
የዚህ አወጋገድ ስርዓትም በተቆጣጣሪ ኤጀንሲዎች በጋራ መከናወን ነበረበት።
ኃላፊነት የተጣለባቸው እነዚህ ኤጀንሲዎችም ክፍት እና ተወዳዳሪ የሆነ ጨረታም ለአጣሪዎች ማውጣት እንዲሁም አስፈላጊ የሚባሉ ግብሮችን እና ክፍያዎችንም መፈጸም ይጠበቅባቸው ነበር።
“ይህንን ተግባር ሊወጡ በሚገባቸው ኤጀንሲዎች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ባለስልጣናት ኃላፊነታቸውን ባለመወጣትም ህዝቡን ለአደጋ አጋልጠውታል” ብለዋል ፊሊክስ ኮስኬይ
የባለስልጣናቱ እገዳ ኬንያውን ለዓመታት አይተውት በማያውቁት ከፍተኛ የስኳር ዋጋ ንረት ካጋጠመበት ወቅትም ጋር ተገጣጥሟል።
