May 22, 2023 – Getachew Shiferaw 

ብልፅግና ኢትዮጵያን እንዲህ ነው የሚፀየፋት፣ የሚጠላት፣ የሚንቃት!

የሚገልፃት በክፋት ነው!

የሚስላት በተንኮል ነው!

የሚፈርጃት በምቀኝነት ነው!

ግለሰቦች መሰል ነገር ሊገጥማቸው ወይንም ከራሳቸው ችግር ተነስተው በስህተት በጅምላ ሊፈርጁ ይችላሉ። ስልጣን ላይ ያለ አካል ይህን ሲል ግን ጠልቶ እንደሚገዛት ማሳያ ነው።

በየትኛውም አገር ምቀኝነት አለ። ተንኮል አለ። ክፋት አለ። በኢትዮጵያም ይኖራል። የህዝብ መገለጫ ግን አይደለም። ህዝብና አገር ግን በእነዚህ ባህሪያት አይጠራም። ደግሞ በገዥ ፓርቲ።

ኢትዮጵያ የስንት በጎዎች አገር ነች። የእነ አበበች ጎበና አገር ነች። ምስኪኖችን ከጎዳና የሚያነሱት የእነ ቢኒያም አገር ነች። በገዳም ስለ ህዝብና አገር እየፀለዩ የሚኖሩ አባቶች አገር ነች። የኃይማኖተኞች አገር ነች። ለአገሩ ሲል መስዋዕትነት የሚከፍል፣ በኢትዮጵያዊነት አምናለሁ እስካለ ድረስ ገዥውን ሳይቀር በርታ የሚል ህዝብ አገር ናት።

ብልፅግና ቂም እንዳለበት ተራ ግለሰብ ነው አገርና ህዝብን የሚፈርጀው። ደግሞስ ክፉትና ተንኮል ከራሱ በልጦ ነው? መጅሊስና ሲኖዶስን እየከፈለ ስለ ሌሎች ክፋት ሊያወራ? ንፁሃንን አልያችሁ እያለ እያፈናቀለ ሌላውን በምቀኝነት ሊፈርጅ?

ይህ ፍረጃ ብቻ አይደለም ችግሩ። መሸታ ቤት እንደሚውል ግለሰብ በጅምላ የሚፈርጅ ተራ አስተሳሰብ የተሸከመ ኃይል ነው ስልጣን ላይ ያለው። አገር የምትመራው በዚህ ውዳቂ አስተሳሰብ ነው።