May 25, 2023 – VOA Amharic

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በሸገር ከተማ “ሕገ ወጥ ግንባታ” በሚል እየተካሔደ ካለው የቤቶች ፈረሳ ጋራ የተያያዙ፣ 100ሺሕ አቤቱታዎች እንደቀረቡለት ሲናገር፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ደግሞ ይህን ያህል ቅሬታ እንዳልቀረበለት ገልጿል።

የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉግሳ ደጀኔ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ “100ሺሕ አቤቱታዎች” የሚለው መረጃ፣ ውይይት ያልተደረገበት፣ በአግባቡ ያልተጣራና ከአንድ ወገን ብቻ የተገኘ ነው፤ ብለዋል፡፡

 የሸገር ከተማ ቤቶች ፈረሳ 100 ሺሕ አቤቱታዎች ቀረቡበት

የሸገር ከተማ ቤቶች ፈረሳ 100 ሺሕ አቤቱታዎች ቀረቡበት

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ግን፣ በጉዳዩ ዙርያ ከከተማዋ ባለሥልጣናት ጋራ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በተቋሙ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ሓላፊ ተወካይ አቶ ተሾመ ያሚ፣ ከሕዝብ ቀረቡ ከተባሉት አቤቱታዎች ጋራ በተያያዘ፣ ከሸገር ከተማ ሓላፊዎች ጋራ ውይይት መደረጉን አረጋግጠዋል፡፡

የሸገር ከተማ አስተዳደር “100 ሺሕ አቤቱታዎች መቅረባቸውን አላውቅም”

By  ቪኦኤ