
ከ 3 ሰአት በፊት
የቻይና የኢንተርኔት መረጃ መንታፊዎች በኬንያ ቁልፍ የሚባሉ የመንግሥት ተቋማት ላይ የመረጃ መረብ ጥቃት አድርሰዋል መባሉን ቻይና አስተባበለች።
በዚህ የመረጃ መረብ ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ቢሮ ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ የመንግሥት ተቋማት ኢላማ ተደርገዋል።
ጥቃቱ ያነጣጠረው ኬንያ ከቻይና የተበደረችውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላሮችን ለመክፈል ያስችል ለመገምገም እንደሆነም ሮይተርስ የዜና ወኪል የዘገበ ሲሆን በኬንያ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ይህንን ክስ አስተባብሏል።
በሮይተርስ ዘገባ መሰረት ለዓመታት የዘለቀው የየመረጃ መረብ ጥቃት በአውሮፓውያኑ 2019 እንደተጀመረ ነው።
ኬንያ ከቻይና የተበደረችው የዕዳ መጠን ማሻቀብ ሲጀምርም ቻይና ይህንን ለመቆጣጠር ክትትል እንደጀመረችም ነው ዘገባው ያስነበበው።
ነገር ግን የቻይና ኤምባሲ ረቡዕ ዕለት በሰጠው መግለጫ ዘገባው “ከእውነት የራቀ እና ከንቱ ነው” ሲል አጣጥሎታል።
“መረጃ ብርበራም ሆነ ጥቃት የሁሉም ሃገራት የተለመደ ስጋት ሲሆን ቻይናም የሳይበር ጥቃት ሰለባ ነች” ሲልም መግለጫው አክሏል።
- የሩሲያን ድንበር ጥሰው የገቡት ሽምቅ ተዋጊዎች ተመሳሳይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ዛቱከ 4 ሰአት በፊት
- የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ ንግሥት ቲና ተርነር በ83 ዓመቷ አረፈችከ 4 ሰአት በፊት
- በዩኬ ለልጃቸው የውሸት አባት ለመግዛት ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፍሉት ስደተኛ ነፍሰጡሮችከ 5 ሰአት በፊት
አንድን መንግስት ያለ ጠንካራ ማስረጃ ለመረጃ መረብ ጥቃት ተጠያቂ ማድረግ በእጅጉ ፖለቲካዊ አላማ ያለው ነው ብሏል ኤምባሲው።
በኬንያ እና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት በመከባበር ላይ የተመሰረተ እንደሆነም ኤምባሲው አጽንኦት ሰጥቷል።
ቻይና ከአውሮፓውያኑ 2000 ጀምሮ ባሉት 20 ዓመታት ትልልቅ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ለአፍሪካ 160 ቢሊዮን ዶላር አበድራለች።
ኬንያ የባቡር መንገድ፣ ወደብና ትልልቅ ጎዳናዎችን ለመገንባት 9 ቢሊዮን ዶላር እንደተበደረችም ከቦስተን ዩኒቨርስቲ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
በዓመታት ውስጥ ኬንያ ከቻይና የምትወስደውን ብድር ቀንሳለች።
እስከ መጋቢት ወር ድረስ ባለውም ኬንያ ከደቡብ ምስራቃዊቷ እስያ ሃገር ቻይና 6.31 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ እንዳለባት ተዘግቧል።