… በሀገራችን ፖለቲካ ታሪክ (በተለይ በዘመነ-ኢህአዴግ እና በዘመነ-ብልጽግና) ከሞት በመለስ ያለውን ሁሉንም ዋጋ ከፍያለሁ። ለሀገሬ፣ ለሕዝቤ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ነጻነትና ለፍትህ የሳሳሁት ነገር ካለ ለማስታወስ ጊዜ ይጠይቃል። በዚህ ቆሻሻ ፖለቲካችን ምክንያት መራብ መጠማትን፣ ማልቀስ ማዘንን፣ መደብደብ መገፋትን፣ መዋረድ መጎሳቆልን፣ ሥራ መከልከል ከሥራ መፈናቀልን፣ የኑሮ፣ የአካልና የሥነልቦና ጉዳትን፣ መታሰር መፈታትን ወዘተ አይቸዋለሁ። አልፌበታለሁ።
ነገር ግን በዚህ ሁሉ መንገድ (በሕይወቴ) እንደ ኢዜማና እንደ ብልጽግና ውስጤን የጎዳ ፓርቲ የለም። በሁለቱም ይህ ነው የማይባል ክህደት ተፈጽሞብናል። በሁለቱም እንደ ሀገርም፣ እንደ ሕዝብም፣ እንደ ዜጋም ተክደናል!
አሁንም ቢሆን የምን ይሻላል? ማብሰለሰል፣ መጨነቅ፣ መጠበብ ይቀጥላል። በዓለም ዙሪያ ያላችሁ የትግል ውዶቼ፣ የዓላማ ጓዶቼ፣ በሕይወት የተረፋችሁም፣ ሕይወት ያጣችሁም፣ የተሰደዳችሁም፣ በየእሥር ቤቱ እየማቀቃችሁ ያላችሁም፣ ሀብት፣ ጤና ወዘተ የተነጠቃችሁ … ፈጣሪና የኢትዮጵያ ሕዝብ የድካማችሁን፣ የድካማችንን መታሰቢያ ያቁም። ሁሌም በውስጤ ናችሁ።
ቻው!

