Habtamu Kitaba
ከአላስፈላጊ ንትርክ ተጠበቁ!
_____
ከኢዜማ የተለየን፤ እንዲሁም ከኢዜማ የተለየነውን የደገፋችሁ ወገኖች በኢዜማ ፓርቲ ዛሬም እምነት ያላቸው ወገኖች ጋር አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ ከመግባት እንድትጠበቁ ከልብ እመክራለሁ።
ኢዜማ ውስጥ ያሉ ወገኖች ተሳክቶላቸው ለአገር የሚጠቅም ሃይል ከሆኑ ጥቅሙ ለሁሉም ነውና የብሽሽቅ ምዕራፍ በፍጹም መከፈት የለበትም። በገባቸው መንገድ መድረስ የሚፈልጉበት ጋር መድረስ መብታቸው ስለሆነ።
ይህ አጋጣሚ ሁላችንም ስለ ፖለቲካ ባህላችን በማሰብና በማንበብ ከውድቀታችን ለመማር የምንሞክርበት መሆን አለበት።
በኢዜማ ቤት ያላችሁ አብራችሁኝ የነበራችሁ ሁላችሁንም ከልብ አመሠግናለሁ። በኢዜማ አካሄድ የምታስቡት ላይ መድረስ እንድትችሉ መሻቴ ነው። በሰላማዊ ትግል፤ በመካከለኛው መንገድ፤ በገዢዎች በፈረቃ እየተገፋ የስልጣኑ ባለቤት መሆን ካልቻለው ህዝብ ጋር በመወገን ራሳችሁን እንድታገኙ ከልቤ እሻለሁ።
መልካሙን ሁሉ!
//ሐኪ
