May 27, 2023 

ኦህዴድ መራሹ ስርዓት በአማራ ክልል እያካሄደ ያለውን መንግስታዊ ሽብር አፈና እና የማገት ተግባር የሚያበረታታ መከላከያ ሰራዊትን እንደግፋለሁ የሚል የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ጠራ !

በደረሰን መረጃ መሰረት መንግስት በህግ ማስከበር ሰበብ በአማራ ክልል እያካሄደ ያለውን የሽብር ተግባር ፋኖን የማሳደድ : የጦር መኮንኖች እና ለአማራው ድምፅ የሆኑትን ጋዜጠኞችና ማህበራዊ አንቂዎች እንዲያስር እና የማሳደዱን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥልበት የፊታችን ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ በተላላኪዎቹ በኩል የድጋፍ ሰልፍ እንዲካሄድ ትእዛዝ ማስተላለፉን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል::

በአዳነች አቤቤ በኩል የተጠራው የአብይ አህመድን የሽብር ተግባር የሚደግፍ ሰልፍ ብዙ የአማራ ተወላጆችን አስቆጡታል::

ዛሬ ቅዳሜ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የአገዛዙ ስርዓት አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት መስጂድ ፈረሰ፣ ቤተክርስቲያን ፈረሰ፣ ፋኖን አትንኩ የሚል ሃሳብ ፈፅሞ ከነዋሪው እንዳይነገር ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፏል።

አሻራ ባጣራው መረጃ መሠረት ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ የትናንቱ የህዝበ ሞስሊሙ ተቃውሞ የአገዛዙን ስርዓት ክፉኛ ስላስደነገጠው በነገው ሰልፍ የማይወጣ የአዲስ አበባ ነዋሪ 5,000 ብር ቅጣ እና እስር እንደሚጠብቃቸው ተናግረዋል።

አሻራ ሚዲያ ፣