
Bedilu Wakjira
ጸሎቴን የማስረዝመው . . . . (በድሉ ዋቅጅራ )
ጊዜ በእድሜ አለንጋ፣
እየገረፈ ‹‹ቼ!›› ሲለኝ፤
እግሬን አልነቅል ብዬ፣
በሬ እንደዋጠ ዘንዶ፣
ለወራት አንቀላፍቼ፣
ከሞት ማምለጥ የሚያምረኝ፤
ጸሎቴን የማስረዝመው፤
መውጫህን
መወጣጫህን
ሳያሳየኝ፣
እንዳይወስደኝ፣
ነው፡፡
ቄጠማ የነበር
አደይ፤
አረንቋና ማጥ የቆምክበት፤
እስከ ቋንጃህ፣
የዋጠህ፤
መርግ ሆኖ፣ ካላሰመጠህ፤
በእድሜህ ሰፍሮ፣ እድሜ እንዲሰጠኝ፤
እስከቆየህ እንዲያቆየኝ፤
ሞቼም ሀሳቡ እንዳይገድለኝ፡፡
ጸሎቴን የማስረዝመው፤
መውጫህን እንዲያሳየኝ ነው፡፡
————–