
በጎጃም የሚገኙ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች እና ሹፌሮች የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ተጠየቀ።
የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 20/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በጎጃም የተክለ ሃይማኖት እና ሥላሴ ገዳም ዛሬም ለአራተኛ ቀን በከባድ መሳሪያ እየተደበደበ ነው ተብሏል።
በጎጀም ደብረ ኤልያስ የተከፈተው ጦርነት ግንቦት 20/2015 አራተኛ ቀኑን ይዟል፤ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ተጨማሪ አምስት ኦራል የኦህዴድ/ኦነግ ሠራዊት ገብቷል።
የኤልያስን ህዝብ ገዳማትን ለሚያፈርሰው የኦነግ ሠራዊት እንጀራ አዋጡ በማለት የከተማው ካድሬዎች እያስገደዱ እንደሆነ ታውቋል።
በዐብይ አህመድ ወራሪ ሠራዊት እስካሁን ድረስ ፀበልተኞች እና መነኮሳት ተገድለዋል፣ ቤተክርስትያን ፈርሷል፣እንስሳት እና ንፁሃን ተሰውተዋል፣አርሶ አደሩ ተንቀሳቅሶ መስራት አልቻለም።
ስለሆነም ከደጀን ጀምሮ እስከ ባህርዳር ድረስ ባስቸኳይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም እና ህዝቡ መንገድ በመዝጋት ገዳማትን እና ንፁሃንን እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።
ከተለያየ አካባቢ ተጭኖ የሚመጣውን የኦነግ መከላከያ የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ እና ገዳማትን እያፈረሰ በመሆኑ ህዝቡ በአካባቢው መንገድ በመዝጋት ገዳማውያንን እንዲታደጉ ተጠይቋል።
ቤተ ክርስቲያን እየፈረሰ፣ንፁሃን የጎጃም አማሮች እየተጨፈጨፉ የተጣለውን የትራንስፖርት እገዳ ጥሶ የሚንቀሳቀስ ሹፌር ምህረት አይደረግለትም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አስጠንቅቀዋል።