May 30, 2023

በብዙ ስራዎቹ የምናውቀው አርቲስት ተሾመ አየለ (ባላገሩ ) በአፋኙ ቡድኑ መታፈኑ ተሰማ

ተሾመ አየለ(ባላገሩ) ትናንት ረፋድ ላይ 4ኪሎ ስላሴ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሠሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል እንደተወሰደ ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።እስካሁን ያለበትን እንደማያውቁም አስረድተዋል።ተሾመ የባላገሩ አስጎብኝ ድርጅት ባለቤት ነው።

ባለገሩ ተሾመ ከአሁን በፊት ፋኖን ታሰለጥናለህ ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ ብሎ ብሎ ነበር። “እኔ የፋኖ መሪ ሳልሆን ፋኖ ነኝ ” የሚል መልስ ሰጥቷቸዋል።
…………
የሀገራችንን ባህልና ትውፊት ለረጅም አመታት በማስተዋወቅ እና 365 ቀን ባህላዊ ልብስ በመልበስ የሚታወቀው የሀገራችን የባህል አምባሳደር ባላገሩ ተሾመ አማራነቱ ቢያሳስረው በሀገራችን ተከስቶ በነበረው የህልውና ዘመቻ ጦርነት ላይ አብሮ ሲሳተፍ በቆየበት ወቅት ያየውንና የተመለከተውን “የሸዋ ተጋድሎ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን የ1:30 ዘጋቢ ፊልም በእምዬ ምኒሊክና በእቴጌ ጣይቱ የልደት ቀንን አስመልክቶ ነሀሴ 12/2014 ዓ/ም በደብረ ብርሀን/ደብረ ኤባ ከተማ በአጤ ምኒሊክ አዳራሽ ማስመረቁ ይታወሳል።

የሸዋ ተጋድሎ የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም ተሾመ ከሽዋ ግንባር እስከ አፋር ከአፋር እስከ አበርገሌ ግንባር ላይ ሆኖ ሲንቀሳቀስ የተመለከተውን ምልከታና እይታ የጻፈው ነበር።
እኔ የፋኖ መሪ አይደለሁም ፋኖ ግን ነኝ ። ፋኖ ደረቱን ለጥይት ሰጥቶ ህይወቱን ለመገበር ለከፈለው መስዋዕትነትና ለሀገር በዋለው ውለታ መሸለም ሲገባው መሳደዱ እና መታሰሩ እጂግ ያሳዝናል። “