May 31, 2023 – Konjit Sitotaw 

ደብረ ማርቆስ ሱቆቿን ዘግታ ትግሉን ተቀላቀለች

የደብረ ማርቆስ ህዝብ በደብረኤልያ የሚደረገው የሥላሳሴ ገዳም የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣የመነኮሳት እና የፀበልተኞች ጭፍጨፈ ባስቸኳይ እንዲቆም ትግሉን ተቀላቅሏል።

ዕምነት የለሹ የዐብይ አህመድ ጨፍጫፊ የኦነግ ሠራዊት ከተቀደሰው የጎጃም ገደማት እና አካባቢዎች ባስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ህዝቡ በቁጣ እየጠየቀ ነው።የማይወጣ ከሆነ ግን ትግሉ አድማሱን አስፍቶ አቅጣጫውን ይቀይራል ብለዋል።

በተመሳሳይ በደጀን፣ቢቸና፣ሞጣ፣አማኑኤል፣ደንበጫ፣ፋኖተ ሠላም፣ቡሬ፣ደንግላ፣መራዊ እና ሌሎች የጎጃም አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ህዘባዊ እምቢተኝነቱን ይቀላቀላሉ ተብሏል።

ማሳሰቢያ፡ ደብረማርቆስ አንድ አንድ የስርዓቱ አገልጋይ ሆቴሎች እና ተሽከርካሪዎች የህዝብን ጥሪ ባለመቀመበል የከፈታችሁ አላችሁ፤ባስቸኳይ እንድትዘጉ እንጠይቃለን።ካልሆነ ለሚደርስባችሁ ጉዳት ኃላፊነቱን እራሳችሁ ትወስዳላችሁ ሲል ህዝባዊ ኮሚቴው አስጠንቅቋል።