30/05/2023 

(Amharic) APF statement

May 29 2023

የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ የኦሮሚያ ልዩሃይል አባላትን የመከላከያ ዩኒፎርም አልብሶ በማሰማራት በአማራ ክልል በደብረ ኤሊያስ ወረዳ አርሶ አደሮች ላይ እና በደብረ ኤልያስ ገዳማትና በመነኮሳት ላይ የሚፈጽመውን ፍጅት መላው ኢትዮጵያዊና የዓለም አቀፋ ሕብረተሰብ
እንዲያወግዘው በጥብቅ እናሳስባለን:: ከስድስት መቶ አመታት በላይ ያስቆጠረው የደብረ ኤሊያስ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በውስጡ ካሉቅዱሳት መጻሕፍት፣ መንፈሳዊ ንዋየ ቅዱሳን እና ታሪካዊ ቅርሶች ለከፍተኛ ጥፉት ተጋልጠዋል::
በአብይ አህመድ የሚታዘዘው ጨፍጫፊው ሠራዊት በዚህ ትልቅ የሀይማኖት እና የባህል ቦታ ላይ
እያደረሰው ያለው የቦምብ ጥቃት ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የዓለም ማህበረሰብንም ሊያሳስብ ይገባል።
አብይ አህመድ የመከላከያ ልብስ አልብሶ ያሰማራው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ከአለም አቀፍ ድንጋጌዎች እና ከወታደራዊ ስነምግባር ውጭ በንጹሃን አርሶ አደሮች እና በገዳማዊ መነኮሳት ላይ እንደ ዙ-23 ሞርታር ዲሻቃ ያሉ ከባድ መትረየሶችን በመተኮሱ በገዳሙ እና በአካባቢው ከ7 ያላነሱ ንፁሀን ዜጎ ህይወታቸውን ለማጣት በቅተዋል። በደብረ ኤልያስ ይህን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ስለመፈጸሙ አገዛዙ እስካሁን ይፋዊ ማብራሪያ ባይሰጥም ከአካባቢው ከደረሰን ተጨባጭ ማስረጃ ተረድተናል።
ፉሽስታዊው የብልጽግ/ኦሮሙማ አገዛዝ ኢንተርኔትና ስልክ አጥፍቶ በደብረ ኤሊያስ የስላሴ ገዳም አብያተ ክርስቲያናት፣ መነኮሳት፣ ተማሪዎች እና በደብረ ኤልያስ ወረዳ ነዋሪዎች ላይ የጦር ወንጀል በከባድ መሣሪያ እየፈጸመ ስለሆነ የዓለም ማህበረሰብ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ በጥብቅ እናሳስባለን።
በተጨማሪም የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ ሆን ብሎ በታሪካዊው የደብረ ኤልያስ ገዳማት እና በወረዳው ኗሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን በከባድ መሳሪያ የታጀበ ከፍተኛ ጥቃት በማውገዝ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተቃውሟችሁን እንድታሰሙ የአማራሕዝባዊ ግንባር (አሕግ) ጥሪውን ያቀርብላችኋል።


መነሻችን የአማራ ሕልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት!