




Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
· በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በማይካድራ እና በሁመራ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሁመራ፡ ግንቦት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሰላማዊ ሰልፉ የማንነት ጥያቄዎች እና የበጀት ጉዳይን በዋናነት መሰረት ያደረገ ነው።
በሰላማዊ ሰልፉ የዞኑ ሕዝብ ለሶስት አስርት ዓመታት ማንነቱ ሳይከበር የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲደርስበት መቆየቱን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል ።
በሰላማዊ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል ።
ወልቃይት እና የአማራ ማንነት ጥያቄን የርስት ማስመለስ ብሎ በመፈረጅ አማራን ማሸማቀቅ አይቻልም! ሀገር ርስት ነው። ለርስት መሞት ክብር ነው
የማይገባንን አልፈን አልጠየቅንም፣ የራሳችንንም አሳልፈን አንሰጥም
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጥምር ጦሩ የከፈለውን መስዋዕትነት እናከብራለን ፣እንዘክራለን ፣ድሉንም እናስቀጥላለን
የአማራን ሕዝብ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት መነጠል አይቻልም፣ መከላከያ የሕዝባችን አቅም፣ የሕዝባችን የመከላከያ ምንጭ ነው የሚሉት ይገኙበታል።