በኮለኔል ፈንታው ሙሃባና ኮለኔል ሞገስ ዘገየ የሚመራው ፋኖ በደቡብ ወሎ ደላንታ ወረዳ ይዞት ከነበረው ወገልጤና ለህዝብ ደህንነት ሲል መውጣቱንና በቅርብ ርቀት ሆኖ እንደሚከታተል በመግለጽ ለነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኮለኔል ፈንታው ሙሃባና ኮለኔል ሞገስ ዘገየ ከሚመራው ፋኖ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሠጠ መግለጫ:_
እንደሚታወቀው በቀን 13/10/2015 ዓም በደቡብ ወሎ ዞን ዴላንታ ወረዳ በተንበኮ ቆላ/ዙ ቆላ ቀበሌ ሊያፍነን በአምስት አቅጣጭ የመጣውን የአብይን ሽፍታ ቡድን በሚያስደምም ጀግንነት ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀን ከፊት የመጣውን ኃይል በቀላሉ ደምስሰን ወገል ጤና ከተማን መቆጣጠራችንን ይታወቃል።
በመሆንም ሽፍታው ቡድን የደረሰበትን ውርደትና ኪሳራ ለማካካስ በማሰብ አምስት ሻለቃ ወይም አንድ ክፍለ ጦር ሰራዊት እንዲሁም ስድስት ዙ-23 ወደ ከተማው መግቢያ በሮች በማስጠጋት እንቅስቃሴዎች መጀመሩ እውን ነበር።
ይህ ኃይል አማራ ጠልና ለአማራ ህዝብና ከተሞች ምንም ርህራሄ የሌለው ፈሪ ግን ጨካኝ ቡድን ለንፁሃን ለሴትና ለህፃናት በአጠቃላይ ሲቪሊያን ላይ በብዙ እጥፍ የሚከፋ ኃይል በመሆኑ ምክንያት እጅግ ብስለት ስክነትና ለህዝባችን እውነተኛ አሌኝታነታችንን ለማሳየት በማሰብ ያለምንም ተኩስ ልውውጥ በኃይል በቀላሉ የተቆጣጠርነውን ከተማ በሰላም ለቀን
በጣም በቅርብ ርቀት እንገኛለን።
ህዝባችን እንዲያውቅልን የምንፈልገው እውነት ተቆጣጥረን የለቀቅነውን ከተማ አይደለም የትኛውንም ከተሞች በፈለግን ሰዓት የመቆጣጠር አቅሙ እንዳለንና የትኛውም ቡድን ሊከለክለን እንደማይችል ማወቅ ግን ይኖርበታል።
በተጨማሪም በየቀበሌውና በየወረዳው ያላችሁ ወጣቶች በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ትግሉን መቀላቀል እየፈለጋችሁ አብረን እንዳንጓዝ እንቅፋቶች ቢበዙብንም በቅርቡ ነገሮችን አስተካክለን እስከምንገናኝ ባለችሁበት ራሳችሁን ለማንኛእም ትግልና የሚሰጣችሁ ግድጅ በደስታ ተቀብላችሁ በቁርጠኝነት ለመፈፀም እንዲያመቻችሁ በአካልም በስነ-ልቦናም እየተዘጋጃችሁ እንደትጠብቁን እያልን በመጨረሻም የወገል ጤና ከተማን ህዝብ ከልጅ እስከ አዋቂ ከተማ ከገባንና ለቀን እስከወጣንበት ሰዓት ድረስ ላሳያችሁን ፍቅርና ክብር እጅግ የላቀ ምስጋናችንን እያቀረበን ባደረጋችሁልን የክብር አቀባበል ትልቅ ባለውለታችን መሆናችሁን በዝች አጭር ፁሁፍ ብቻ መግለፅ ንፉግነት እንዳይሆንብን እየጠየቅን ለቀጣይ ህዝባችን ለማይቀርለት የሞት ሽረትና የህልውና ትግል ራሱንና የራሱን እንዲሰጥ እንጠይቃለን::
“ኃይላችን ያለው ፋኖ ከሚለው ታላቁ ስማችን ላይ ነው”
ኮለኔል ፈንታው ሙሃባ
ኮለኔል ሞገስ ዘገየ
ቀን 18/10/2015 ዓም
