July 9, 2023 – Konjit Sitotaw 

በአፋር ቡሬ ማንዳ ወታደራዊ ካምፕ ፣ በቀን እስከ 10 የሚደርሱ የግፍ እስረኞች ፣ በረሀብና በህክምና እጦት እየሞቱ እንደሚገኙ ተገለፀ!

በአፋር ክልል ቡሬ ማንዳ በሚባል ስፍራ ከሚገኝ የመከላከያ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ፣ በተለይም ከመከላከያና ከፌደራል ፖሊስ አማራ በመሆናቸው ብቻ ”ፋኖ ናችሁ! ፋኖን ትደግፋላችሁ!” እየተባሉ ከየአካባቢው ተለቅመው እጅግ በርካቶች ለወራት ታስረው ይገኛሉ።

ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገና ከስፍራው ያለ የመረጃ ምንጬ << ታሳሪዎቹ እንደእሳት በሚፋጀው በረሀ ላይ እጅግ አሰቃቂ በሚባል ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ እየተሰቃዩ ታስረው የሚገኙ ሲሆን ፣ ምግብና ውሃ እንዲሁም ህክምና ባለማግኘታቸው ምክንያት ብቻ በየቀኑ እየረገፉ ሲሆን በቀን በአማካኝ እስከ 10 የሚደርሱ የግፍ ታሳሪዎች በረሀብና በህክምና እጦት እየሞቱ ይገኛሉ! >> ሲል ተናግሯል ።

<< ለእናንተ ጥይት አናባክንም ፣ ተሰቃይታችሁ ትሞቷታላችሁ ! >> እንደሚባሉ የገለፀው የመረጃ ምንጬ ፣ በረሀብ ከመሞት በማለት ለማምለጥ ሙከራ ያደረጉም በየእለቱ እንደሚረሸኑ አስታውቋል።

በተመሳሳይ መልኩ ከቀናት በፊት ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ታፍነው ተወስደው ፣ በአፋር ክልል – ከኤርትራ 42 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ” በሱላ ወታደራዊ ካምፕ ” በእስር ላይ የሚገኙት በርካታ አማራዎች በረሀብ እና በህክምና እጦት ህይወታቸውን እያጡ እንደሚገኙ መዘገቡ የሚታወስ ነው።

ድምፅ እንሁናቸው ቢያንስ የተረፉትን ሰሚ ካገኘን! ዘሪሁን ገሰሰ