July 9, 2023 – Konjit Sitotaw 

መንግስት የመርሐቤቴ አርሶ አደሮችን በመፈንቅለ መንግስት ከሰሰ

የፌደራል መንግስት “መፈንቅለ መንግስት ሊያደርጉብኝ ነው፣ ህገ መንግስቱንም በሀይል ሊንዱብኝ ነው” በማለት የመርሐቤቴ አርሶ አደሮችን ከሰሰ። አርሶአደሮቹ ወደ እርሻ እየሄዱ ሳለ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ ተብለው ወደ ኦሮምያ ክልል ተወስደው ነበር።

እነዚህ አርሶ አደሮች ወደ ኦሮምያ ተወስደው ከታፈኑ ከሳምንት በኋላ ወደ አዲስአበባ ፌደራል ፖሊስ ተወስደዋል። አርሶአደሮቹ የአማራክልል ነዋሪዎች ሆነው ሳለ ወደ ኦሮምያ ክልል ለምን እንደተወሰዱ የታወቀ ነገር የለም። በሰ/ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩት አርሶ አደሮቹ እስር ላይ በመሆናቸው በዚህ ዓመት ለቀጣይ የሚሆን ቀለብ ለማረት አለመቻላቸውን ሲያሥቡ እጅግ ማዘናቸውን ገለፀዋል፡፡

ከመርሐቤቴ አርሶ አደሮች በተጨማሪም የቀወት ወረዳ እና የሸዋሮቢት ከተማ አርሶ አደሮች ና ነጋዴዎችም ወደ ኦሮምያ ክልል ተወስደው ታፍነው ነበር፡፡ እነዚህ አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች ወደ ኦሮምያ ከዛም ወደ አዲስ አበባ የተወሰዱት በምን ምክንያጥ እንደሆነ እንዳልተነገራቸው ገልፀዋል፡፡ ዕድሜያቸውን በትክክል ማወቅ ያልቻሉት አንድ የመርሐቤቴገበሬ “ለምን እንደተያዥኩ አላውቅም ነበር።

በኋላ ላይ ህገመንግስቱን በሃይል ለመናድ ስትንቀሳቀስ ነበር አሉኝ፣ እኔ ደግሞ አረ እኔ ወደ እርሻ ስንቀሳቀስ ነበር፣ የልጆች አባ ነኝ ወ ስራ እየሄድኩ ነው ብላቸውም ” አማራ መታሰር አለበት፣ማረስና መስራት የለበትም፣ ነፍጠኞች መነቃቀል አለባቸው። እናንተ እያላችሁ ሰላም የለም አሁን ጊዜው የኦሮሞ ነው” እንዳሏቸው ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ከታሰሩ 30 ቀና አልፈዋል፡፡ ፍ/ቤት ዋስ ቢላቸውም ፖሊስ አልፈታም ብሎ አሁንም ወህኒ ቤት የገኛሉ፡፡