July 10, 2023 – Konjit Sitotaw

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልኡካን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀሌ አመሩ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የተመራ የሰላም ልኡካን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀሌ ከተማ አምርቷል።
የሰላም ልኡኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአገር ሽማግሌዎች ያካተተ መሆኑን የቤተክርስቲያኒቷ የመገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
በዕለቱም ብፁዕ አቡነ አርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጀና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ተገኝተው ለቅዱስ ፓትርያርኩና ለልኡካኑ ሽኝት ማድረጋቸው ተገልጿል።