
ከ 3 ሰአት በፊት
በቻይናዋ ደቡብ ምስራቅ ግዛት ጓንግዶንግ በተፈጸም የስለት ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገደሉ።
ከሟቾቹ በተጨማሪም አንድ ሰው መቁሰሉንም ፖሊስ ለቢቢሲ ተናግሯል።
ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ አንድ የ25 ዓመት ወጣትን ፖሊስ ማሰሩን ገልጿል።
በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈው አንድ አስተማሪ፣ ሁለት ወላጆች እና ሦስቱ ደግሞ ተማሪዎች ናቸው ተብሏል።
ጥቃቱ ዛሬ [ሰኞ] ማለዳ ላይ የተፈጸመ ሲሆን ፖሊስ ጥቃት አድራሹን በደቂቃዎች ልዩነተ በቁጥጥር ሥር አውሏል።
ፖሊስ ጥቃቱ “ሆን ተብሎ የተፈጸመ ነው” ብሏል።
- የሱዳን ተፋላሚ ወገኖችን ለማቀራረብ አዲስ አበባ ላይ ውይይት ሊጀመር ነውከ 4 ሰአት በፊት
- እነ ቲክቶክ በአሜሪካ ድንበር የሕገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር እንዲስፋፋ እያደረጉ ነውከ 5 ሰአት በፊት
- በጀርመን የኤርትራ ፌስቲቫል ላይ በተከሰተ ግጭት 26 ፖሊሶች ሲጎዱ 100 ኤርትራውያን ታሰሩ9 ሀምሌ 2023
በቻይና እንደዚህ አይነት ጥቃቶች በብዛት የሚፈጸሙ አልነበሩም። በዚህ ዓመት ግን በተለይ የስለት ጥቃት በትምህርት ቤቶች ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶች በብዛት ተከስቷል።
ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር አንድ ግለሰብ መዋዕለ ሕጻናት ግቢ ውስጥ በስለት በፈጸመው ጥቃት ሦስት ሰዎች ሲገደሉ፣ ስድስት ሰዎች ደግሞ ቆስለው ነበር።
በፈረንጆቹ 2021 በተመሳሳይ ጥቃት ቤይሉ በተባለች የቻይና ከተማ 2 ሕጻናት ተገድለው 16 ሰዎች ቆስለው ነበር።