July 10, 2023 

የትግራይ ክልል ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ መቅደስ ዘግተው ጠፉ፤ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ በዝግ ተወያዩ፤ 

++++

* ለሰላም ውይይት የተጠበቁት ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያንን በር ዘግተው ጠፉ፤

* መድረክ ያመቻቻል ተብሎ የተጠበቀው ጊዜያዊ አስተዳደሩ “ጣልቃ አልገባም” አለ፤

** ዶ/ር ደብረ ጽዮን፣ ቅዱስ ፓትርያርኩን በዝግ አነጋገሩ፣

++++++

(አደባባይ ሚዲያ፣ )፦ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅራዊ አንድነት የማጠናከር እና ሰብአዊ ርዳታ የማድረስ ተልእኮ በመያዝ፣ ዛሬ ሰኞ፣ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ጠዋት ወደ ትግራይ ክልል ያቀናው፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የተመራ የሰላም ልኡክ፣ የጉዞው ዓላማ የሆነው በትግራይ የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን የማግኘቱ ጉዳይ እንዳልተሳካ ተገለጸ፡፡

+++