
ከ 4 ሰአት በፊት
የቡድን 7 ሃገራት ረዥም ጊዜ የሚቆይ ለዩክሬን የሚሆን ልዩ የደኅንነት ማዕቀፍ በኔቶ ስብሰባ ላይ ይፋ ሊያደርጉ ነው።
ማዕቀፉ የጦር መሣሪያ፣ ሥልጠና እና የደኅንነት መረጃ ማጋራትን ያካትታል።
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እንዳሉት ስምምነቱ ለፕሬዝደንት ፑቲን “ጠንካራ መልዕክት” ያስተላልፋል።
ይህ የሆነው የዩክሬን ፕሬዝደንት ዜሌንስኪ፤ ኔቶ የኪየቭን የመቀላቀል ጥያቄ ችላ ብሏል ብለው ወቀሳ ካሰሙ በኋላ ነው።
ጠ/ሚ ሱናክ እንዳሉት ምዕራባዊያን ወዳጆች “ዩክሬንን ለመጠበቅ ረዥም ጊዜ የሚቆይ ስምምነት ይገባሉ።”
“ዩክሬን ውስጥ የተፈጠረው ነገር ድጋሚ ሲሆን ማየት የለብንም። አዲሱ ድጋፍ ሩሲያ የምታደርሰውን በደል ብቻዋን ስትወጣው ማየት እንደማንሻ ማረጋገጫ ነው።”
- አፍሪካን እና አፍሪካውያንን ብዙ እያሳጣቸው ያለው እጅግ ውዱ የአየር ቲኬት ዋጋከ 6 ሰአት በፊት
- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም “ጉልህ ክፍተቶች” እንዳሉበት ተጠቆመ11 ሀምሌ 2023
- በኔቶ ጉባኤ የዩክሬን የወደፊት የኅብረቱ አባልነት ጉዳይ አንዱ መወያያ እንደሚሆን ተገለጸ11 ሀምሌ 2023
አክለው ዩክሬን ኔቶን እንደትቀላቀል ድጋፍ ማድረግና የኔቶ ሃገራት በጋር የሚያደርጓቸው ጉዳዮች ለሩሲያው ፕሬዝደንት ግልፅ መልዕክት ያላቸውና “አውሮፓ ወደ ሰላም እንድትመለስ” የሚያግዙ ናቸው።
የጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ጽ/ቤት በለቀቀው መግለጫ ዩናይትድ ኪንግደም ለስምምነቱ መሳካት መሪ ሚና ተጫውታለች ብሏል።
ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን እና ዩኤስ ያሉበት የኃያላን ቡድን ረቡዕ ዕለት ተጨማሪ መረጃ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እንደጠቆሙት ለዩክሬን ሊሰጥ የታሰበው አሜሪካ ለእስራኤል ካደረገችው ጋር ተመሳሳይነት አለው።
በዚህ ስምምነት መሠረት አሜሪካ ለአስር ዓመት የሚቆይ በየዓመቱ 3.8 ቢሊዮን ዶላር የደኅንነት ድጋፍ ለእስራኤል ታደርጋለች።
ነገር ግን ይህ ስምምነት ልክ እንደ ኔቶ አባል ሃገር ሲተነኮስ እርዳታ ማድረግ የሚል አልተካተተበትም።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን [ኔቶ] “አባላት ከተስማሙና ሁኔታዎች ከተሟሉ” ዩክሬን መቀላቀል ትችላለች ይላል። ዜሌንስኪ ይህ መዘግየቱ “ግራ አጋቢ” ነው ይላሉ።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጦርነት ገጥማ ሳለች ቃል ኪዳኑን መቀላቀል እንደማትችል ብትረዳም ጦርነቱ እንደተገባደደ አባል መሆን ትሻለች።
ማክሰኞ ዕለት በሉቱዌኒያ ዋና መዲና ንግግር ያደረጉት የዩክሬኑ መሪ “ኔቶ ለዩክሬን ደኅንነት ይሰጣል። ዩክሬን ደግሞ ድርጅቱን ጠንካራ ታደርገዋለች” ብለዋል።
ቱርክ እምቢኝ በማለቷ ምክንያት ኔቶን መቀላቀል ከብዷት የነበረችው ስዊድን አሁን መልካም ዜና ሰምታለች።
አሁን አንካራ አቋሟን በማለሰላሷ ሰዊድን በቅርቡ የቡድኑ 32ኛ አባል ትሆናለች።
ባለፈው ሚያዚያ ከሩሲያ ድንበር የምትጋራው ፊንላንድ የቃል ኪዳኑ አዲስ አባል መሆኗ ይታወሳል።
ሁለቱም ሃገራት ኔቶን ለመቀላቀል ጥያቄ ያቀረቡት ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ነው።