
ከ 5 ሰአት በፊት
ሰሜን ኮሪያ አህጉር ተሻጋሪ ባለስቲክ ሚሳዔል ሳትተኩስ እንዳልቀረ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ገለጹ።
ረዥም ርቀት ተጓዡ ሚሳዔል አንድ ሰዓት ከተጓዘ በኋላ የጃፓን ድንበር አካባቢ ካለ ውሃ ረቡዕ ጠዋት ወድቋል።
ፒዮንግያንግ ይህን ሙከራ ያደረገችው አሜሪካ ሰላይ አውሮፕላን ይዛ ወደ ድንበሬ ዘልቃ ገብታለች የሚል ወቀሳ ካቀረበች በኋላ ነው።
ሰሜን ኮሪያ ከዚህ በኋላ መሰል አውሮፕላኖችን መትታ እንደምትጥል ዝታለች።
አሜሪካ ወቀሳውን አጣጥላ ወታደራዊ አውሮፕላኖቼ ዓለም አቀፍ ሕግን ተከትለው ነው የሚበሩት ብላለች።
ሰሜን ኮሪያ በያዝነው ዓመት በርካታ የሚሳዔል ሙከራ ማድረጓን ተከትሎ በአካባቢው ያለው ውጥረት አይሏል።
- በኔቶ ጉባኤ የዩክሬን የወደፊት የኅብረቱ አባልነት ጉዳይ አንዱ መወያያ እንደሚሆን ተገለጸ11 ሀምሌ 2023
- ምዕራባውያን አገራት አሜሪካ ክላስተር ቦምቦችን ለዩክሬን ለመላክ መወሰኗ አሳሰቢ ነው አሉ9 ሀምሌ 2023
- የኮሎምቢያው ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ከ60 ዓመታት ጦርነት በኋላ ለተኩስ አቁም ተስማማ5 ሀምሌ 2023
ዩናይትድ ስቴትስና ደቡብ ኮሪያ በጋር የሚያካሂዱትን ወታደራዊ ሥልጠና አጠናክረው ቀጥለዋል።
ይህ ፒዮንግያንግ ላደረግችው በርካታ ሙከራና የጦር መሣሪያዋን አቅም ለማሳደግ ቃል ለመግባቷ ምላሽ ይመስላል።
ባለፈው ሚያዚያ ሰሜን ኮሪያ እስከዛሬ ካመረተቻቸው መሣሪያዎች “እጅግ ኃይለኛው” ያለችውን ‘ሶሊድ ፊዩል’ የሚጠቀም አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳዔል ሞክራለች።
ባለፈው ረቡዕ ሰሜን ኮሪያ የሚሳዔል ሙከራ ካደረገች በኋላ ጎረቤቶቿ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ወዲያ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
ሚሳዔል አየር ላይ እየተመዝገዘገ ሳለ ነው ባለሥጣናቱ ረዥም ርቀት ተጓዥ መሣሪያ እንደሆነ የጠረጠሩት።
ከፒዮንግያን በምስራቅ አቅጣጫ ከአንድ ሰዓት በላይ ከተምዘገዘገ በኋላ ጠዋት 5፡15 ግድም ለጃፓን የሚቀርብ ባሕር ላይ መውደቁን የሃገሪቱ ድንበር ጠባቂ ኃይል ገልጧል።
ሰሜን ኮሪያ ለመጨረሻ ጊዜ የሚሳዔል ሙከራ ያደረገች ባለፈው ሰኔ አጋማሽ ነው። ያኔ ሙከራው ለአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ሥልጠና ምላሽ ነበር።
ነገር ግን የካቲት ላይ ደግሞ አህጉር ተሻጋሪ የባለስቲክ ሚሳዔል ሙከራ አድርጋ ነበር።
አህጉር ተሻጋሪ ባለስቲክ ሚሳዔል አሳሳቢ የሚሆነው የአሜሪካ ግዛቶች ድረስ ተጉዞ ሊወድቅ መቻሉ ነው።
ሰሜን ኮሪያ በፈረንጆቹ ኅዳር 2022 የሚሳዔል ሙከራ ስታደርግ ከፍ በሎ የሚበርና አጭር ርቀት የሚጓዝ ሚሳዔል ነበር።
ነገር ግን በወቅቱ የጃፓን ባለሥልጣናት ይህ የጦር መሣሪያ ዝም ብሎ ቢበር የአሜሪካ ግዛቶች ሊደርስ ይችላል የሚል አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም።