
ከ 2 ሰአት በፊት
ሰሜናዊ ምዕራብ አፍሪካ እና የደቡብ አውሮፓ ግዛቶች በከፋ የሙቀት ማዕበል ተመቱ።
በመጪዎቹ ቀናትም በታሪክ ከፍተኛው የተባለው የሙቀት መጠንም ሊመዘገብ እንደሚችል ተጠብቋል።
በአንዳንድ የስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ክሮሺያ እና ቱርክ የሙቀት መጠኑ ከ40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ከፍ እንደሚልም ተተንብይዋል።
በጣሊያን የሙቀት መጠኑ እስከ 48.8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደሚደርስ ሲጠበቅ ፍሎረንስ እና ሮምን ጨምሮ በአስር የጣሊያን ከተሞች ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ማክሰኞ ዕለት በሰሜን ጣሊያን ነዋሪ የነበረ በ40ዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ግለሰብ በሙቀት ምክንያት ራሱን ስቶ ህይወቱ አልፏል።
የ44 ዓመቱ ግለሰብ በሚላን አቅራቢያ በምትገኘው ሎዲ ከተማ መንገድ ቀለም እየቀባም እያለ ነው በሙቀት ምክንያት ተዝለፍልፎ የወደቀው። ግለሰቡን ከወደቀበት አፋፍሰው ወደ ሆስፒታል ቢወስዱትም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።
“ልንቆጣጠረው የማንችለው የሙቀት ማዕበል ገጥሞናል” በማለት ጣሊያናዊው ፖለቲከኛ ኒኮላ ፍራቶያኒ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
- በናይሮቢ በተደረገ የአደባባይ ተቃውሞ ከ50 በላይ ሕጻናት ተጎድተው ሆስፒታል ገቡከ 4 ሰአት በፊት
- ጣሊያናዊቷ ታዳጊ የደረሰባት ወሲባዊ ትንኮሳ ከ10 ሰከንድ በታች ነው መባሉ ቁጣ ቀሰቀሰከ 4 ሰአት በፊት
- ወሲባዊ ይዘት ላላቸው ፎቶዎች ከፍሏል የተባለው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ሆስፒታል ገባከ 4 ሰአት በፊት
“ከፍተኛ ሙቀት በሚያጋጥሙ ሰዓታት ውስጥ ጠቃሚ የሚባሉ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ዛሬ በሎዲ ውስጥ እንደተፈጸመው አሳዛኝ ሁኔታን ለመከላከል ሊረዳ ይችላል” ሲሉም አክለዋል።
በርካታ አገሪቷን እየጎበኙ ያሉ ቱሪስቶች በሙቀት ማዕበሉ ምክንያት ተዝለፍልፈው ወድቀዋል።
የጣሊያን ሜትሮሎጂ ማህበር ጣሊያናዊው ጸሃፊ ዳንቴ አሊጌሪ ኢንፌርኖ በተሰኘው ግጥም ውስጥ ሶስት ጭንቅላት ያለው ጭራቅ- ሴርቤሩስ ሲሉም የሙቀት ማዕበሉን ሰይመውታል።
የሙቀት ማዕበሉ በሚቀጥሉት ቀናትም በጣም የከፉ ሁኔታዎችን ሊያስከትል እንደሚችልም ይጠበቃል።
የሜትሮሎጂ ጽህፈት ቤት አርብ ላይ የሙቀት መጠኑ ከፍተኛ እንደሚሆን ሲተነብይ የቢቢሲ የአየር ጸባይ ትንበያ በኩሉ ደቡባዊ የአውሮፓ ግዛቶች ዝቅተኛው የተባለው እስከ 40ዎቹ አጋማሽ እንዲሁም ከፍ ያለ ሙቀት ያጋጥማል ብሏል።