
ከ 4 ሰአት በፊት
አንድ ታዳጊ ወሲባዊ ይዘት ያለው ፎቶግራፍ እንዲልኩ ገንዘብ ከፍሏል በሚል ከሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ የነበረው ጋዜጠኛ ማንነት ይፋ ሆኗል።
በዚህ የተወነጀለው ለአራት አስርት ዓመታት በቢሲ በጋዜጠኝነትና አቅራቢነት እያገለገለ ያለው ሂው ኤድዋርድስ መሆኑን የተናገረችው ባለቤቱ ናት።
ባለቤቱ ጋዜጠኛው ሂው ኤድዋርድስ “በከባድ የአዕምሮ ጤና ጉዳዮች” ምክንያት ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኝ በተናገረችበት መግለጫዋ ነው ከዚህ ውዝግብ ጀርባ ያለው ባለቤቷ መሆኑን የጠቀሰችው።
ዘ ሰን የተባለው ጋዜጣ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ወሲባዊ ይዘቶች ያላቸው ፎቶዎችን እንዲልኩ ለማድረግ ለአንድ ታዳጊ ስለመክፈሉ ዘገባ ማውጣቱን ተከትሎም ከሰሞኑ የጋዜጠኛው ማንነት አነጋጋሪ ሆኖ ነበር።
ቢቢሲ የግል የመረጃ መብታቸው ጋር ይጣረሳል በሚል የአቅራቢውን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥቦ ነበር።
ባለቤቱ ቪኪ ፍሊንድ ጋዜጠኛውን በመወከልም ይህንን መግለጫ እንድትሰጥ ምክንያት የሆናት “በዋነኛነት ለእምሮ ጤንነቱ እና ልጆቻችንን ለመጠበቅ በማሰብ ነው” ብላለች።
የቢቢሲ የቴሌቪዥን መርሃ ግብር አቅራቢ አንድ ታዳጊ ወሲባዊ ይዘት ያለው ፎቶግራፍ እንዲልኩ መክፈላቸውን በመጀመሪያ የዘገበው ዘ ሰን ጋዜጣ ነው።
ማንነታቸው እንዲሁም ፆታቸው ያልተገለጸው ጋዜጠኛ ማንነታቸው እንዲሁም ፆታቸው ያልተገለጸ ታዳጊን ከ17 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ልቅ ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ፎቶዎች እንዲልኩ በአስር ሺህ ፓውንዶች የሚቆጠር ገንዘብ መክፈላቸውን የጋዜጣው ሪፖርት ይጠቁማል።
ፖሊስ በበኩሉ ወንጀል እንዳልተፈጸመና የ61 ዓመቱ ጋዜጠኛ ምንም ዓይነት የወንጀል ምርመራ እንደማይከፈትበት አረጋግጧል።
ጋዜጠኛው ጤናው ሲስተካከል ለቀረበበት ክስ ማብራሪያ እንደሚሰጥም የቤተሰቡ መግለጫ አክሏል።
- የቢቢሲ ጋዜጠኛ ወሲባዊ ይዘት ላላቸው ፎቶዎች ለታዳጊ መክፈላቸው ተጠቆመ8 ሀምሌ 2023
- ወሲባዊ ይዘት ካላቸው ፎቶዎች ጋር በተያያዘ በታገዱት ጋዜጠኛ ዙሪያ የቢቢሲ ኃላፊ ምላሽ እንደሚሰጡ ተጠቆመ11 ሀምሌ 2023
- የተባበሩት መንግሥታት ኤድስን በቀጣዮቹ ሰባት ዓመታት ውስጥ ከዓለም ማጥፋት ይቻላል አለከ 5 ሰአት በፊት
“የቢቢሲ ጋዜጠኛን በተመለከተ በቅርብ የወጡ ዘገባዎችን መሰረት በማድረግም ነው ባለቤቴን ሂው ኤድዋርድስን ወክየ ነው መግለጫ የምሰጠው። ዜናው ከወጣ በኋላ የተከተሉት አምስት ቀናት ለቤተሰባችን እጅግ ፈታኝ እለታት ሆነዋል። ይህንን መግለጫ የምሰጠው በዋነኝነት ለአምሯዊ ደህንነቱ እንዲሁም ልጆቻችንን ለመጠበቅ ነው” ብላለች።
“ሂው በከባድ የአዕምሮ ጤና እክሎች እየተሰቃየ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከከፋ የድባቴ ህመም ጋር በተያያዘ ህክምና እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል” ብላለች።
“ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የተከሰቱ ሁኔታዎች የአዕምሮ ጤና እክሉን በእጅጉ አባብሰውታል።በአሁኑ ወቅትም የከፋ የጤና እጅል ገጥሞትም በሆስፒታል ውስጥ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል” ስትል አስፍራለች።
ለአራት አስርት ዓመታት በቢቢሲ ጋዜጠኝነት የሰራው ሂው ኤድዋርድስ በተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ ደመወዝ ከሚከፈላቸውም አንዱ ነው። በአውሮፓውያኑ 2022፣ 435 ሺህ ፓውንድ እንዲሁም በ2023፣ 439 ሺህ 999 እንደተከፈለው መረጃዎች ያሳያሉ። ጋዜጠኛው ከባለቤቱና ከአምስት ልጆቹ ጋር በለንደን ይኖራል።