Mengistu Musie
የህወሓት እና የኦነግ
የፖለቲካ ፍልስፍና ዳርቻው የት ይሆን?
———————————-
ምናልባት ጨርሶ ሁሉንም እርስ በእርስ ተጫርሶ ማለቅ?
ነው ሁለቱም እንደተመሰረቱበት ሌላውን ወንድማቸውን/እህታቸውን ጨርሰው እነሱ በሰላም መኖር?
——————————–
ወይንስ ልክ እንደዚህ ለሁለት አመታት እንደተካሄደው ጦርነት ከየሰሜኑ ሌላ የደቡ ወይንም የምስራቅ አጋር መፈለግ እና አንዱ ሌላውን ለመጨረስ ሌላ ዙር ጦርነት ማካሄድ?
——————————————-
መጠፋፊያ መሰረታዊ አላማ ያረጉት ሁለቱም ኢትዮጵያን አጥብቀው መጥላታቸው ነው።
እናም ኢትዮጵያን ለማጥፋት ደግሞ ሕዝቧን በዘር መከፋፈል እና ጠላት ማድረግ ነበር። ይህ ተፈጽሟል ተሳክቶላቸዋል፤
ሌላው ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታሪካዊ ጠላቶቿ ማየት የማይፈልጉትን አርማዋን ዳብዛ ማጥፋት ነበር። ይህም ተሳክቶላቸዋል – ሰንደቋ የተፈጠረችበት መቀሌ ዛሬ አንድም የሰንደቅ ምልክት ሊኖር ክልክል ነው። ሚኒሊክ እና ኃይለስላሴ ጠላቶቻቸውን በሕዝባቸው ተጋድሎ ድል አድርገው ሲመለሱ በድል የተውለበለባት አዲስ አበባ ይዞ መገኘት ወንጀል ሆኗል። ታዲያ ይህም የነጻነት አርማዋን ማጥፋቱም ተሳክቶላቸዋል ሌላ ምን ቀረ?
———————-
ለኢትዮጵያ እና ሕዝቧ በክፉ እና በደግ አስተባብራ ይዛ የኖረች ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ነበረች። ይህችን ቤተክርስቲያን ለመንካት ፈጽሞ አይሞከርም ያልነውን ያህል ዛሬ ትግራይ እና ኦሮሞያ የዚህች ቤተክርስቲያን ፍዳ በሰርጎ ገብ መነኩሳት ውጊያ ደከመች። አክሱም ጺዮን የመጀመሪያዋ መሰረት በህወሓት ተዘጋ እናት ቤተክርስቲያንንም ለሁለት ዳግም ከፈሏት። ሌላ ምን ቀረ?
——————————
እስልምናን በጸጋ የተቀበለች ሀገራችን ዛሬ ከ 1600 አመታት በሁኋላ በእስልምናም ላይ መስጊድ በማፍረስ የሚካሄደው ዘመቻ ቀጥሏል። ሌላ ምን ቀረ? ለኢትዮጵያዊነት ዋና መሰረት ያልናቸው ሁሉ አንድ በአንድ በአይናችን እያመለጡን ነው። ህወሓት/ኦነግ ከዚህ ሁሉ መተላለቅ ሕዝባችንን የመኖር አንጡራ ሐብቱን ገፈው። አገሩን አስለቅቀው ከፊሉን መዳረሻ አሳጥተው ወደውጭ የተሰደደውን ብንተው አንዴ የውጭ ስደተኛውስ ላይመለስ ሌላ ተስፋው ደብዝዟል የሐገር ውስጥ ስደተኛው መዳረሻ ባጣበት በዚህ ዘመን አሁንም የጦርነት እና የጥላቻ ዘማቾች ምን ቢቀራቸው ምን ፈልገው ይሆን?
—————————————-
ሲመሰረቱ በወረቀት ያሰፈሩት የፖለቲካ ፕሮግራማቸው ሁሉም ተፈጻሚ ሆኗል። የዘመቱባት ሐገር፤ የዘመቱበት ሕዝብ ሁሉም ባሰቡት ተፈጻሚ ሆነ። የትግራይ አብያተ ክርስቲያናት በራቸውን ዘጉ፡፤ ጥላቻ አካለመጠን ደርሳ እና ጎልብታ እና ገዝግዛ ኢትዮጵያዊነትን መገፍተርሯን ብሎም ለመጨረሻው ግብ መቃረቧን ያላወቀ በምድራችን ሊኖር አይችልም።
ህወሓት/ኦነግ ግባቸው ይህ ነው ግን ገና ይህም አይበቃቸውም።
ከኢትዮጵያ መጨረሻስ ምን ሊፈጥሩ? እነሱም እኛም፤ ሐገራችንም ወዴት እንደምናመራ ግልጽ አይደለም። እርግጠኛው ነገር ግን ቆሻሻው የዘር ፖለቲካቸው ለጥፋት ዳር እና ዳርቻ አለመኖሩን እያየን ነው። ከዚህስ በኋላ 50ኛ አመቱን ያከበረው “ጥላቻ” የሚሉት የነዚህ ሁለት ድርጅቶች ብርቅየ ፍጡር ከኢትዮጵያ ውጭ የትም ሊገባ አይችልም የፈረደባትን አገር አኝኮ ከበላ በኋላ መጨረሻው እራሱን መብላት እራሱን ማጥፋት መሆኑ መቸም ሳይታለም የተፈታ ነው! እኛም እግዞ እንበል። ለሐገራችን ለወገኖቻችን ከምንግዜውም በላይ እንጨነቅ። የጥላቻ አይን ከዚህ ሁሉ መጠፋፋት በሁአላ አፎቱን አላዞረምእና፡