July 13, 2023 – Abebe Bersamo 

በወልቃይት ጉዳይ ላይ ዶር አብይ አህመድ ከተወሰኑ የአማራ ክልል አመራሮች ጋርና  ከህወሃት ሰዎች ጋር በተናጥል ስብሰባ ማድረጉ በስፋት ተዘግቧል፡፡ ከህወሃቶች ጋር ባደረገው ውይይት፣ እነ ወቅላኡይትን ህወሃቶች እንዲረከቡ ፍላጎት እንዳለው የገለጸላቸው ሲሆን፣ በፌዴራል መንግስት ደረጃ የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል መግባቱን አንከር ሜዲያ ዘግቧል፡፡ አንከር ሜዲያ ሲያክልም፣ አማራዎች ፍቃደኛ ካልሆኑ፣  እና እዚህ እናዳክምላቹሃልን፣ በስንቅ በትጥቅ እናግዛቹሃለን፣ ራሳችሁ በጦርነት ያዙ” የሚል አስተያየት እንደሰጡም አትቷል፡፡

የቻልኩትን አድርጋለሁ ባለው መሰረትም፣ የአማራ ክልል ሃላፊዎችን በመሰብሰብ  ማስፈራሪያና ዛቻ አዘል መመሪያዎች ለመስጠት ሞክሯል፡፡ ከአብይ አህመድ ጋር የተመካከሩትና የተስማሙት የአማራ ክልል አመራሮች አምስት እንደነበሩ ኢትዮ ኒዉስ ዘግቧል፡፡ እነርሱም የክልሉ ርእስ መስተዳደርና ምክትል ርእስ መስተዳደር፣ ዶር ይልቃል ከፍያለ እና ዶር ጌታቸው ጀምበር፣ ዶር ሰማ ጥሩነህ፣ የደቡብ ጎንደር አስተዳዳሪ የነበረውና ለአብይ አህመድ ባለው ትልቅ ታማኝነት፣ አሁን ግርማ የሺጣላን ተክቶ የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ሃላፊ የሆነው አቶ ሲሳይና ፣ አቶ ስዩም መኮንን ናቸው፡፡

በዚህ ስብሰባ አብይ አህመድ ቀጭን ትእዛዝና መመሪያ አስተላልፎላቸዋል፡፡ “በወልቃይት ጠገዴና ቃፍታ ሁመራ፣ በጠለምትና በራያ የዘረጋችሁት የአማራ ክልል መስተዳደር ጠራርጋችሁ አስወጡ” የሚል፡፡ እነ ወልቃይትን ምእራብ ትግራይ በሎ በመጥራት ፣ ከዚያ የተፈናቀሉ በሙሉ እንዲመለሱ መመሪያ ሰጥቶ ፣ ተፈናቃዮችንም በተመለከተ፣ በስብሰባው የተገኙ የአማራ አመራሮች አሜን ብለው ተቀብለዋል፡፡ይህ ብቻ አይደለም፣ እነዚህ የአማራ ክልል አመራር ነነ የሚሉትን ህወሃቶች በፈለጉት መንገድ ፣ ህዝብ ውሳኔ የተባለውን ተቀብለው ለመተግባር ቃል ገብተዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ኮሎኔል ደመቀ አስተያየት እንደሰጡ ኢትዮ ኒዉስ ዘግቧል፡፡ “የአማራ ክልል መንግስት ስላደረጋቸው ንግግሮች እኛ የምናወቀው ነገር የለም፡፡ እኛ የጉዳዩ ባላቤቶች ሆነን ሳለ፣ ሃሳብ ስጡ ተብለን አልተጠየቅንም” ሲሉ የተናገሩት ኮሎኔል ደመቀ፣ “የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ፣ የአማራ ህዝብ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን ይወቅልን፡፡ ለሚሆነውን ነገር በሙሉ ተጠያቂ አንሆንም” በሚል ራሱን የክልሉ መንግስት ነኝ ብሎ በሚጠራውና፣ በአብይ አህመድ ኦህዴድ መዳፍ ውስጥ በወደቀው አመራር ያላቸውን ትልቅ ቅሬታ አሳውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል መንግስት ከበስተጀርባ በህዝብ ላይ ታላቅ ክህደት እየፈጸመ ነው የምንለው በዚህ ምክንያት ነው፡ ይህ ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ አንድ ወቅት እንኩቶ፣ ሌላ ወቅት ትርፍ አንጀት ብለው የጠሩት ስብስብ፣ የሳር ውስጥ እባብ ሆኖ፣ የአማራ ማሀብረሰብ ላይ እጅግ በጣም አደገኛ ደባ እየፈጸመ ስለመሆኑን ማሳያ ነው፡፡

ለአንድ ሚሊዮን ህዝብ እልቂት ምክንያት የሆነውን ጦርነት የቀሰቀሱት ህወሃቶች፣  እንደገና ለኣማራ ክልል ስጋት እየሆኑ እንዲጠናከሩ ያደረጉት አራት ኪሎ ያሉ የኦህዴድ ገዢዎች ናቸው፡፡ እነ አብይ አህመድ፣ የደቡብ አፍሪካው ስምምነት መሰረት ትጥቅ እንዳይፈቱ አድርገው፣  በመሳሪያ፣ በሎጂስቲክ፣ በስንቅ አስፈላጊዉን ድጋፍ እየሰጧቸው፣  ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ፣ በተለየም ወደነ ጠለምት ፣ ራያና ወልቃይት አዋሳኝ ቦታዎች በመከላከያ መኪናዎች የህወሃት ታጣቂዎችን እንዲመላለሱ እያደረጉ፣ የመከላከያ  ዩኒፎርም አልብሰው ፣ እነ ወልቃይትን ፣ “መከላከያ ይቆጣጠራል” በሚል ህወሃቶችን ለማስገባት እየሰሩ ነው፡፡

እነ አብይ አህመድ በዚህ ልክ ፣ በተለይም የአማራ ክልል ህዝብን እንዲያሸብሩ፣ እንዲያምሱ ፍቃድ መስጠት ብቻ አይደለም፣ እየተባበሩ ያሉት ደግሞ  ራሳቸውን የአማራ ክልል መንግስት  ወይም የአማራ ብልጽግና  ነን ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች ናቸው፡፡ እነዚህ የኦህዴድ ታማኝ አገለጋዮች፣  ህዝብን እየካዱ፣ የኦህዴዶች በትርና ዱላ ሆነው፣  ህዝቡን እየደበደቡ፣ በህዝብ ላይ ክህደት እየፈጸሙ ነው፡፡  በየአምራ ክልል ከተሞች በአብይ ት እዛዝ በአስር ሺሆች ፋኖዎች አስረዋል፡፡ በየቢታ መመሪያ ተቀብለው ፋኖን ትጥቅ እናስፈታለን በሚል የክልሉን ሚሊሺያን ፖሊስ እየላኩ አስቸግረዋል፡፡ በአንዳድን ቦታ እርምጃ የተወሰደባቸው ቢሆንም፡፡ አብይ አዟቸው የአማራን ማሀብረሰብ እንደ ጠላት ቆጥሮ፣ ለአራተኛ ዙር ጦርነት እየተዘጋጀ ያለውን፣ በአማራ ጥላቻ ሊወጣ ያልቻለውን የዘረኛ ቡድን መሪን በቀይ ምንጣፍ በባህር ዳር ተቀብለዋል፡፡ ከህወሃቶችም ጋር አብረ መደነስ ጀምረዋል፡፡

ይሄንን ደግሞ እያደረጉ ያሉት ህዝብ ፈቅዶላቸው ነው፡፡ ህዝብ የነርሱን ውሸትና ማማለል፣ “እኛም እኮ የናንተ ወንድሞች ነን፣ በሽምግልና እንፍታው ወዘተ” እያሉ በሚያደርጉት ማታለልና ማዘናጋት በ እጅጉ ተታሎና ተወናብዶ፣ እነርሱ ላይ ቀይ መስመር ማስመር ባለመቻሉ ነው፡፡

የአብይ አህመድ ተረኛው የኦህዴድ አገዛዝ በተለይም በአማራው ማህበረሰብ ላይ የፈጸመው ግፍና ሰቆቃ የሚታወቅ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ጦርነት ከፍቶ ህዝብን እየጨረሰ ያለው ይህ ክፉ ናዚዛዊ አገዛዝ ነው፡፡ የአራት ኪሎ መንግስት የህዝብ ጠላት ነው፡፡ ከዚህ ከህዝብ ጠላት ጋር የቆመን፣ “አብሮ አደጌ ነው፣ የወንዜ ልጅ ነህ፣ አብሬው ተምሪያለሁ፣ እንደኔው አማራ ነው፣ እንደኔው ጎንደሬ ወይ ጎጃሜ ነው፣ ወይንም እንደኔ በጣም ወርዶ ደግሞ ከጋየንት ነው፣ ከአሸፈር ወዘተ በሚል  ማለፍ ትልቅ ዋጋ እያስከፈለ ነው፡፡  ከአብይ አሀመድ ናዚዛዊ ኦህዴድ  ጋር የሚሰሩ  የሕዝብ ጠላት ናቸው፡፡ አራት ነጥብ፡፡

ስለዚህ ነገሮች ለማጠቃለል፣ ሄዶ ሄዶ፣  በህወሃትም ሆነ በናዚዛዊ የአብይ አገዛዝ፣  በአማራ ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ሰቆቃ ለመቀጠሉ ምክንያት፣ ለህወሃቶችና ለነ አብይ አህመድ ጥንካሬና ጉልበት ፣ የሆነው የአማራ ብልጽግና የሚባለው  ስብስብ ነው፡፡ ይህን ሁሉም በደንብ መረዳትና ማወቅ አለበት፡፡ የአማራ ብልልጽግና የሚለው ስም፣ ብልጽግና የሚለው ቃል ወጥቶ፣ “የአማራ መርገምት” በሚል መተካት ነው ያለበት፡፡ ለምን ሰዎቹ  ለህዝቡ ብልጽግና ሳይሆን መርገምት ያመጡ በመሆናቸው፡፡

እዚህ በአንዲት ነጥብ ልቋጭ፡፡ በአማራ ብልጽግና ውስጥ ለህዝብ የቆሙ እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግለሰቦች ለህዝብ ቢቆሙም፣ ድርጅቱ እንደ ድርጅት፣ የክልሉ መንግስት እንደ እንድ ክልል መንግስት እያደረገ ያለውን ነው ማየት የሚያስፈልገው፡፡ በድርጅቱም ሆነ በክልሉ መንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ፣ ድርጅታቸው በውስጥ ትግል በአስቸኳይ መስመሩን እንዲያስተካክል ካላደረጉ፣ ለቀው መውጣት ነው የሚኖርባቸው፡፡