
16 ሀምሌ 2023, 08:48 EAT
የደቡብ ኮሪያ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በጎርፍ ከተጥለቀለቀ የአስፋልት ዋሻ ውስጥ 8 አስክሬኖችን አውጥተዋል።
በሃገሪቱ የጣለው ከባድ ዝናብ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት እና የኃይል መቆራረጥ አስከትሏል።
እስካሁን ቢያንስ 26 ሰዎች ሲሞቱ 10 ሰዎች ደግሞ የት እንደደረሱ አይታወቅም።
685 ሜትር በሚረዝመው ዋሻ ውስጥ በትንሹ 15 መኪናዎች የታጨቁ ሲሆን አሁንም በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው ሊያልፍ ይችላል የሚል ስጋት አለ።
የኦሶንግ አውራጃ አስተዳዳሪዎች እንደሚሉት ዋሻው በጎርፍ የተጠቅለቀለቀው በአቅራቢው የሚገኘው ወንዝ ሞልቶ በመፍሰሱ ነው።
ደራሽ ውሃ በፍጥነት በመምጣቱ ዋሻው ውስጥ የነበሩ መኪናዎች ራሳቸውን ማዳን አልቻሉም።
እሑድ ጠዋት የስድስት ሰዎች ሬሳ አውቶቡስ ውስጥ ተገኝቷል።
አንድ ተጨማሪ ሬሳ ዋሻው ውስጥ ሲገኝ ዘጠኝ ሰዎች ደግሞ ከአደጋው ተርፈዋል።
የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በጠቅላላው በተፈጥራዊ አደጋው ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 33 ነው ይላሉ።
- የደብረ ብርሃን ከተማ ፖሊስ አዛዥ ባልታወቁ ሰዎች ተገደሉ15 ሀምሌ 2023
- በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን አምክነዋል በሚል በሐሰት የተከሰሱት ዶክተር16 ሀምሌ 2023
- በሕጋዊ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እንዴት ማቅናት ይቻላል?15 ሀምሌ 2023
በርካታ ሞት በመተዘገበባት ሰሜን ጊዮንግሳንግ የመሬት መንሸራተት ቤቶችን እየጠራረገ ወስዷል።
ቅዳሜ ዕለት 300 ሚሊ ሊትር የሚለካ ዝናብ በመላው ደቡብ ኮሪያ ጥሏል።
ደቡብ ኮሪያ በዓመት የምታገኘው ዝናብ መጠን ከ1 ሺህ እስከ 1 ሺህ 800 የሚለካ ሲሆን አብዛኛው በክረምት ወራት የሚጥል ነው።
ከሰማይ የተነሱ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት ሃገሪቱ ቡናማ መልክ ባለው ውሃ ተከባለች። ቤቶች ተውጠው አናታቸው ብቻ ነው የሚታየው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃን ዳክ-ሱ የሃገሪቱ ጦር ሠራዊት ወደ አደጋ ጊዜ ሥራ እንዲሰማራ አዘዋል።
አርብ ምሽት በመሬት መንሸራተት ምክንያት አንድ ባቡር ፉርጎዎን ለቆ ወጥቶ የባቡሩ ኢንጂነር ጉዳት ደርሶበታል። በወቅቱ ባቡሩ መንገደኞች አላሰፈረም ነበር።
የኮሪያ ሜቴዎሮሎጂ አስተዳዳር እስከሚቀጥለው ረቡዕ ድረስ ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል ይችላል ሲል ተንብይዋል።
አስተዳደሩ አክሎ የሚጥለው ዝናብ ከባድ ስለሆን “አደጋ ሊያደርስ ይችላል” ብሏል።
ኮሬይል የተባለው የሃሪቱ ባቡር ጣቢያ ቀርፋፋዎቹ ባቡሮችና አንዳንድ ‘ቡሌት ትሬን’ የሚባሉ ፈጣን ባቡሮዝ ለጊዜው ሥራ ማቆማቸውን ይፋ አድርጓል።
የአየር ጠባዩ ከፍተኛ አደጋ ስለደቀነ ሥራ መሥራት እንዳልቻለ የባቡር ጣቢያው ገልጧል።
በደቡብ ኮሪያ ብቻ ሳይሆን በሕንድ፣ ቻይና እና ጃፓንም እንዲሁ ባለፉት ቀናት ከባድ ጎርፍ ተከስቷል።
በሙቀት ሳቢያ የምድር ከባቢ አየር ቅዝቃዜ መያዝ ስለማይችል ከባድ ዝናብ እንዲጥል ምክንያት ይሆናል።