
ከ 27 ደቂቃዎች በፊት
ቻይና ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ በምጣኔ ሃብት ለማገገም እየጣረች ባለችበት ወቅት ከፍተኛ የወጣቶች የሥራ አጥነት ቁጥር መጨመር ገጥሟታል ተባለ።
የመንግሥት መረጃ እንደሚያሳየው ከ16 እስከ 24 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶች የሥራ አጥነት ቁጥር ባለፈው ወር በ21.3 በመቶ ከፍ ብሏል።
የዓለም ሁለተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ የሆነችው ቻይና እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ ባሉት ሦስት ወራት ያሳየችው እድገት 0.8 በመቶ ብቻ ነው።
ተንታኞች እንደሚሉት አዝጋሚ የሆነውን እድገት ለማነቃቃት ባለሥልጣናት ምናልባትም አዲስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ እየገለጹ ነው።
የቻይና ስታቲስቲክስ ቢሮ እንዳለው ግን የምጣኔ ሃብት እድገቱ ከነበረበት ሁኔታ ለማገገም በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን ያሳያል ብሏል።
- እናት እና አራት ልጆቿን ጨምሮ 13 ሰዎች የሞቱበት የትራፊክ አደጋ በሰሜን ሸዋከ 1 ሰአት በፊት
- የኢራን የሞራል ፖሊስ ሂጃብ በማይለብሱ ሴቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ መልሶ ሊጀምር ነውከ 3 ሰአት በፊት
- ትዊተር በኢላን ከተገዛ በኋላ ከማስታወቂያ የሚያገኘው ገቢ በግማሽ ቀነሰከ 3 ሰአት በፊት
ሰኞ ዕለት በወጣው መረጃ መሠረት በሁለተኛው ሩብ ዓመት የቻይና ኢኮኖሚ በ6.3 በመቶ እድገት አሳይቷል።
በመላው ዓለም የቻይና ሸቀጦች ፈላጊያቸው ቀንሷል። የምጣኔ ሃብት ሙያተኞች እንደሚሉት በዚህ ዓመት 11.58 ሚሊዮን ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ሥራ እንደሚገቡ ይናግራሉ።
በከተማ የወጣቶች የሥራ አጥነት ቁጥር ለረጅም ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ለዚህ አንደኛው ምክንያት ተማሪዎች የተማሩበት የትምህርት ዘርፍ እና ገበያ ላይ የሚገኘው የሥራ ዘርፍ አለመመሳሰል ነው። የሥራ አጥነት ቁጥሩ በነሐሴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እስከሚደርስ ድረስ እንደሚቀጥል ባለሥልጣናት አምነዋል።
ባለሙያዎች እንደሚገምቱት በቻይና በከተሞች 1.4 በመቶ መሥራት የሚችል ኃይል ሥራ አጥ ሆኗል።
ቻይና የወጣቶች የሥራ አጥነት መረጃን መግለጽ የጀመረችው በፈረንጆቹ በ2018 ነው። ነገር ግን በገጠር አካባቢዎች ያለውን የሥራ አጥነት መጠን እስካሁን መመዝገብ አልጀመረችም።
በመጋቢት ወር የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ የአገሪቱን ዓመታዊ 5 በመቶ ዕድገት ለማሳካት ተጨማሪ ጥረቶች ማድረገግ ይገባል ማለታቸው ይታወሳል።
ምንም እንኳ ምጣኔ ሃብቱ እየተረጋጋ እና እያደገ ቢሆንም ዕቅዱን ማሳካት ግን ቀላል እንደማይሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ባለፈው ወር የሰዎችን የመግዛት አቅም ለማበረታታት ማዕከላዊ ባንኩ የወለድ መጠንን ቀንሷል። ነገር ግን ሙያተኞች እንደሚሉት ኢኮኖሚውን የበለጠ ለማሟሟቅ መንግሥት ተጨማሪ እርምጃዎችን መውሰድ ይኖርበታል።