
18 ሀምሌ 2023, 07:33 EAT
ለወትሮው አንድ ስልክ ከሱቅ ከወጣ ያለው ዋጋ ያሽቆለቁላል። ነገር ግን በአሜሪካው ጨረታ የታየው ሌላ ነው።
የመጀመሪያው የአይፎን ዘር የሆነው ከሰገባው ያልወጣ ስልክ 190 ሺህ 372 ዶላር ከ80 ሳንቲም ተሽጧል።
ይህ ገንዘብ አሁን ባለው የውጭ ምንዛሪ ተመን ብንመታው ከ10.4 ሚሊዮን በላይ ብር ነው።
4ጂቢ የተባለው የአይፎን ምርት ለገበያ ሲበቃ በገፍ አልነበረም። ለዚህ ነው የአይፎን ሰብሳቢዎች ይህን ምርት ማግኘት የሚያጓጓቸው።
28 ሰዎች ስልኩን ለመግዛት ተሽቀዳድመው በስተመጨረሻውም ከተገዛበት ዋጋ 400 እጥፍ ተሸጧል።
የመጨረሻው ዋጋ በጨረታ ቋንቋ የመዶሻ ዋጋና ሌሎችንም ወጭዎች ያካተተ ነው።
ጨረታውን ያካሄደው ድርጅት ይህ የአይፎን ምርት በተጫራቾች እጅግ የሚፈለግ ምርት እንደሆነ ይናገራል።
ባለፈው ዓመትም እንዲሁ ድርጅቱ ከካርቱናቸው ያልወጡ፤ የታሸጉበት ፌስታል ያልተላጠ የአይፎን የመጀመሪያው ምርት ስልኮች በከፍተኛ ዋጋ እንደተሸጡ ድርጅቱ ይገልጣል።
የድርጅቱ ድረ-ገፅ ይህን በ1999 አሊያም በፈረንጆቹ 2007 ለገበያ የቀረበውን ምርት ለመግለፅ ቃላት ያጥረዋል።
“እጅግ ልዩ የሆነ፣ ያልተላጠ – ያልተፈቀፈቀ፤ የመጀመሪያው የ4 ጂቢ ምርት፤ በልዩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ፤ እንከን የማይወጣለት፤. . .” ሲል ድረ-ገፁ ላይያስተዋውቃል።
- በቤተ-ሙከራ የተሠራ ሥጋ የሚሸጥበት ብቸኛው የዓለማችን ሬስቶራንት18 ሀምሌ 2023
- ‘ብላክ ሚረር’ እንደተሰኘው የኔትፍሊክስ ፊልም የሆሊውድ ተዋንያን መልክና ድምፅን ‘ኤአይ’ ይተካው ይሆን?16 ሀምሌ 2023
- ማይክሮሶፍት የአሜሪካ ባለሥልጣናትን የመልዕክት ልውውጥ በመጥለፍ ቻይናን ከሰሰ13 ሀምሌ 2023
ይህ የአይፎን ምርት ለገበያ በበቃ ወቅት የመሸጫ ዋጋው 599 ዶላር ነበር።
ለጨረታ ሲቀርብ ደግሞ ቢበዛ ከ50-100 ሺህ ዶላር ያወጣል የሚል ግምት ነበር። ነገር ግን ክብረ-ወሰን በሰበረ ዋጋ ሊሸጥ ችሏል።
ይህ የአይፎን ምርት መጀመሪያ በ1999 ለዓለም ሕዝብ ይፋ ሲሆን የአፕል ዋን ሥራ አስከያጅ ስቲቭ ጆብስ ነበሩ ያስተዋወቁት።
ነገር ግን የ4ጂቢ ስልክ ገበያው ብዙም አልነበረም።
ሽያጩ የቀዘቀዘበት አፕል ከሁለት ወራት በኋላ ይህን ምርት ለማቋረጥ ተገዷል።
በምትኩ በርካታ ሰዎች 8ጂቢ የተባለውን ተመሳሳይ ሰዓት የተመረተ ሞዴል ወደውት እሱን ይሸምቱ ጀመር።
8 ጂቢው 100 ዶላር የዋጋ ጭማሪ ቢኖርበትም አንደኛው የተወደደበት ምክንያት የተሻለ ቋት [ስቶሬጅ] ስለነበረው ነው።
በየጊዜው ብዙም የማናያቸው የአፕል ምርቶች አሊያም የስቲቭ ጆብስን ሕይወት የሚያሳዩ ዕቃዎች ለጨረታ ይቀርቡ ጀምረዋል።
ለምሳሌ ጆብስ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ የፃፈው ግጥም አሊያም የተነሳው ፎቶ፤ በፈረንጆቹ 1978 ያሳተመው ‘ቢዝነስ ካርድ’ ለጨረታ ቀርበዋል።
ከኦፕል መሥራቾች አንዱ የሆነው ስቲቭ ጆብስ በፈረንጆቹ 2011 ነው በጣፊያ ካንሰር ምክንያት ይህችን ዓለም የተሰናበተው።
አይማክ ኮምፒውተር፣ አይፖድ፣ አይፓድና አይፎን የስቲቭ ጆብስ ውጤቶች ናቸው።