May be an image of text

Yidnekachew Kebed

  · ለጠቅላላ እውቀት የVPN ጠቀሜታ !

VPN ምንድን ነው??

VPN = Virtual Private Network

ይህ ዘዴ አንድ ሰው ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ የኢንተርኔት አገልግሎትን እንድናገኝ የሚረዳ ነው። በዚህ ዘዴ የኢንተርኔት አገልግሎትን መጠቀም ተጠቃሚውን ከሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እይታ በመሰወር ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በነጻነት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኝ ይረዳዋል። VPN በምንጠቀም ግዜ የምንልከውና የምንጠቀመው ዳታ በኮድ ስለሚታሰር ሌላ አካል በመካከል ገብቶ መልክት እንዳይጠልፍ ያደርገዋል።

እንዴት ይሰራል?

ለምሳሌ በአደባባይ/public Wi-Fi ላይ ደህንነት ይፋዊ Wi-Fi ለአጠቃቀም ምቹ ነው። ነገር ግን በደህንነት ረገድ እጅግ ተጋላጭ ያደርጋል። በምትኖርበት አካባቢ ፣ ካፌ ፣ መዝናኛ ፣ ኤርፖርት ፣ ወዘተረፈ ያሉ ቦታዎች ባሉ የአደባባይ ዋይፋዮች ማህበራዊ ሚዲያ ወይም ሌላ ስትጠቀም ፣ የሆነ የመረጃ መንታፊ አካል በቀላሉ የአንተን መገኛ ቦታና እንቅስቃሴዎች እንዲከታተል ያስችለዋል። ይህም በቀላሉ ተጠቂና ተጋላጭ ያደርግሀል። ቪፒኤን ከተጠቀምክ ግን ይህ ሁሉ ችግር ይቀረፋል። መረጃዎችህና የምትጠቀመው ኔትወርክ የግልም ሆነ የአደባባይ ስጋት አይኖርብህም።

ሁላችንም ከኢንተርኔት ጋር የምንገናኘው የኢንተርኔት አቅራቢ ደንበኞቻችን በሚሰጡን የ ip አድራሻ በኩል ነው። ይህ ልዩ የሆነ አድራሻ ከእያንዳንዳችን ኢንተርኔት መጠቀሚያ መስመሮች የሚላኩትን መለዕክቶች እና ኢንተርኔት ላይ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የኢንተርኔት ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡን አካላት እንዲከታተሉ አስፈላጊ ከሆነም ገደብ እንዲጥሉ ይረዳቸዋል።

VPN ኮኔክት አድርገን ኢንተርኔት ለመጠቀም በምንሞክርበት ጊዜ የ ip አድራሻችንን ይሰውረዋል ። ይህም የሚሆነው VPN ኑ የተለመደውን የኢንተርኔት አቅጣጫ በመቀየር ከኢንተርኔት አገልግሎት ሰጭያችንቁጥጥር ውጭ ወደ ሆነ የመረጃ ቋት ስለሚያደርሰን ነው በዚህ መንገድ ያለማንም ሶስተኛ ወገን ታልቃ ገብነት እና እገዳ ኢንተርኔትን መጠቀም ይቻላል። በዚህ ጊዜ የምናደርጋቸውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢው (ለምሳሌ ቴሌ) ሊቆጣጠረው አይችልም ማለት ነው።

ምን ይጠቅማል??

virtual private network/VPN ለግልም ሆነ ለቢዝነስ የበይነመረብ ግንኙነቶች ከሚሰጣቸው በርካታ ጥቅሞች መካከል አንደኛው የ VPN ጥቅም ደህንነቱ የተረጋገጠ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ ማስቻሉ ነው። በኢንተርኔት አማካኝነት የተለያያ ዳታዎች በምንለዋወጥ ግዜ ምንም አይነት የመረጃ መንጠባጠብ ( Data leakage) እንዳይኖር በማድረግ በኩል ይኸ ዘዴ ትልቅ ሚና አለው። ሌላው ደሞ በየአካባቢው የተገደቡ መረጃዎችን ለማግኘትም ይረዳናል( ለምሳሌ መንግስት ተብየው የዘጋቸው ድረገጾችንም ማግኘት እንችላለን)። እነዚህን መረጃዎች ለማግኘት የግድ በተፈቀሰው ክልል በአካል መገኘትን ሳይጠይቅ በ VPN አማካኝነት መረጃዎቹን አክሰስ ማድረግ ይቻላል።

ለምሳሌ በሀገራችን በተለይም ማህበራዊ ሚዲያዎች በተለያየ ምክንያት ገድውብ በሚጣልባቸው ግዜ ሰዎች VPN በመጠቀም አገልግሎት ሊያገኙ ይችላሉ ማለት ነው።