የቫግነር ተዋጊዎች

19 ሀምሌ 2023, 11:53 EAT

የሳተላይት ምሥሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተሽከርካሪዎች የቫግነር ቅጥረኛ ወታደሮችን ጭነው ቤላሩስ ሲገቡ አሳዩ።

ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት ከቤላሩስ መዲና ሚኒስክ 103 ኪሎ ሜትር ርቆ ወደሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ የቫግነር ተዋጊዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በብዛት ገብተዋል።

ይህ ወታደራዊ ካምፕ የቫግነር ታጣቂዎች እና የሩሲያ መንግሥት እርቅ ከመፈጸማቸው በፊት ባዶ እንደነበር የሳተላይት ምስሉ አሳይቷል።

ቫግነር በፕሬዝዳንት ቱፒን አስተዳደር ላይ የቀሰቀሰው አመጽ ከከሸፈ በኋላ የተዋጊ ቡድኑ አባላት ወደ ቤላሩስ እንዲገቡ ተደርጓል።

በቅርብ የተነሱ የሳተላይ ምስሎች በስምምነቱ መሠረት ቫግነር በብዛት ወደ ቤላሩስ እየገባ መሆኑን አሳይተዋል። ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት በሁለት ሳምንታት ውስጥ ‘ጼል’ ተብሎ በሚጠራው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ቢያንስ 300 ድንኳኖች ተዘርግተዋል።

በሌላ በኩል ቫግነር በመልዕክት መለዋወጫ የቴሌግራም ቻናሉ ላይ በደቡብ ሩሲያ ከሚገኘው ዋናው የሥልጠና ማዕከሉ ላይ አርማው መውረዱን ገልጿል። አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ አርማን የማውረድ ልምድ ከወታደራዊ ማሠልጠኛ ቦታ መዘጋት ጋር ይያያዛል።

ማክሰኞ ዕለት የሩሲያ አጋር የሆኑት የቤላሩስ መሪ አሌክሳንደር ሉካሼንኮ፣ ቫግነር በአሁኑ ወቅት በአገራቸው ካምፕ ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

“የወገኖቻችንን አስከሬኖች እየተሻገርን ነው ሳዑዲ የገባነው” ኢትዮጵያውያን ስደተኞች19 ሀምሌ 2023

ራማፎሳ፡ ቭላድሚር ፑቲንን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ማሰር ጦርነት ማወጅ ነው19 ሀምሌ 2023

ከቱፓክ ግድያ ጋር በተያያዘ ፖሊስ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ብርበራ አካሄደ19 ሀምሌ 2023

የቫግነር ተዋጊዎች የተለያዩ መስመሮችን በመጠቀም ወደ ቤላሩስ እንደገቡ የሳተላይት ምስሉ አመልክቷል።

ወደ ካምፑ ሲያመሩ በበርካታ ተሽከርካሪዎች የተጫኑት የቫግነር ወታደሮች፣ የሩሲያን እና የራሳቸውን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለቡ እንደተጓዙ በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ምስሎች ያሳያሉ።

አሁን ጼል ወደተባለው የቤላሩስ ወታደራዊ ካምፕ የገቡት የቫግነር ተዋጊዎች ቁጥር በውል አይታወቅም።

የቤላሩስ የምርመራ ዘገባ አቅራቢው ሃይን ሚዲያ እንደሚለው ከሆነ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ የቫግነር አባላት ወደ ቤላሩስ የገቡ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከ600 በላይ ሰዎች ወደ ካምፑ መግባታቸውን ይገምታል።

ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ ደግሞ ባለፈው ሰኞ ብቻ ወደ ካምፑ ቢያንስ 30 ተሽከርካሪዎች ገብተዋል። እነዚህ ተሽከርካሪዎች ግን የጫኑት ወታደር ይሁን ጦር መሳሪያ የታወቀ ነገር የለም።

ቫግነር በሩሲያ ጦር ላይ ካመጸ በኋላ ወዲያውኑ እርቅ ተፈጸሟል። ይህንን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ፑቲን በሰጡት መግለጫ የቫግነር ቡድን አባላት የሩሲያን ጦር መቀላቀል ወይም ደግሞ ከመሪያቸው የቭጌኒ ፕሪጎዢን ጋር ወደ ቤላሩስ መሻገር እንደሚችሉ አማራጭ አስቀምጠውላቸው ነበር።