July 20, 2023 – Konjit Sitotaw 

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች ደህንነት ላይ ለሀገር የማይተካ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው አርቲስት ደበበ እሸቱ በኪነጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት ውለታ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እያካሄደ ባለው ምረቃ ላይ ደግሞ ለድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዕውቅናው ሁለገቧ አርቲስት #የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነ ጥበብ #የአዊን_ሕዝብ_ቋንቋ እና #ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላት።

የክብር ዶክትሬቱን የእጅጋየሁ ሽባባው ወላጅ እናት ተቀብለዋል።