
ከ 2 ሰአት በፊት
የኒው ዚላንድ የፍትሕ ሚንስትር ኪሪ አለን አልኮል ጠጥተው ማሸከርከራቸው በመረጋገጡ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥራ ተሰናበቱ።
የፍትሕ ሚንስትሯ ሲያሸከረክሩት የነበረው መኪና ግጭት ከደረሰበት በኋላ በተደረገ የትንፋሽ ምርመራ የአልኮል መጠጥ መውሰዳቸው ተደርሶባታል።
ይህንን ተከትሎም ሚንስትሯ ወዲያውኑ ተፈጻሚ የሚሆን በገዛ ፍቃድ ከሥራ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
የ39 ዓመቷ ኪሪ አለን በግዴለሽነት በማሽከርከር እና በፖሊስ ላለምታሰር በመገዳደር የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ባለፈው እሁድ ሌሊት በደረሰው የሚንስትሯ የመኪና ግጭት የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።
ከባለፈው መጋቢት ወዲህ በጠቅላይ ሚንስትር ክሪስ ሂፕኪንስ ካቢኔ ውስጥ ሥራ የሚለቁ ሚንስትሮች ቁጥር አራት ደርሷል።
አደጋውን ተከትሎ ሚንስትሯ ለአራት ሰዓታት ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በእስር ያሳለፉ ሲሆን ወደፊት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከፍትሕ ሚንስትርነታቸው የለቀቁት አለን በሕዝብ እንደራሴ አባልነታቸው እንደሚቀጥሉ ግን ጠቅላይ ሚንስትር ሂፕኪንስ ገልጸዋል።
ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ ‘ጃ’ በዓለም አቀፉ ምናብ23 ሀምሌ 2023
ትዊተር አርማውን ከምናውቃት ወፍ ወደ ‘ኤክስ’ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ኢላን መስክ ገለጠከ 5 ሰአት በፊት
አንድ ሚሊዮን ዶላር ቤታቸው ተገኝቷል የተባሉት የጋናዋ ሚኒስትር ሥልጣን ለቀቁከ 4 ሰአት በፊት
ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም “በተለይም እንደ ፍትህ ሚንስትርነቷ እንዲህ አይነቱ ወንጀል የማይጠበቅ በመሆኑ በሥራዋ ለመቀጠል ሞራል የሚያሳጣ መሆኑን ተረድታለች” ብለዋል።
ተሰናባቿ ሚንስትር ከአሁን በፊትም በተለያዩ የሚንስቴር መሥሪያ ቤቶች ያገለገሉ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ በግል ጉዳይ ምክንያት እረፍት ወስደው ወደ ሥራ ገብታቸው የተመለሱት ባለፈው ሰኞ ነበር።
ሚንስትሯ ባለፈው ወር ከትዳር አጋራቸው ጋር መለያየታች ያሳወቁ ሲሆን ከቀርብ ግዜ ወዲህ በሥራ ገበታም ከባልደረቦች ጋርም ደካማ ግንኙነት እንደነበራቸው ተገልጿል።
አለን በሰጡት መግለጫ “ትናንት የፈጸምኩት ነገር የሚያሳየው ጥሩ እንዳልነበርኩ ነው” ያሉ ሲሆን ቀጣይ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ አስብበታለሁ ብለዋል።
አለን በአንድ ወቅት የሌበር ፓርቲ እንቁ ሴት ተደርገው ይታዩ ነበር። እንዲያውም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ስልጣን የለቀቁትን ጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደንን ይተካሉ ተብሎ ነበር።
ጠቅላይ ሚንስትር ሂፕኪንስ እንደሚሉት በቅርቡ የታወቀው ችግር የአለን መልቀቅ ቢሆንም በአጠቃላይ ፓርቲያቸው ውስጥ ግን ቀውስ ተፈጥሯል ብለዋል።
በሚቀጥለው ጥቅምት ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ባለፈው ሚያዚያ የተደረገው የሕዝብ አስተያየት መቀበያ በገዥው ሌበር ፓርቲ እና በዋነኛ ተቀናቃኙ ናሽናል ፓርቲ መካከል ብርቱ ፉክክር እንደሚደረግ አሳይቷል።