
ከ 2 ሰአት በፊት
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ ነው አለ።
ኢሰመኮ በጋምቤላ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዙ ግጭቶች ሲከሰቱ መቆየታቸውን እና በዚህ ሳቢያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየደረሱ መሆኑን ገልጿል።
በቅርቡ ደግሞ ከግንቦት 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ኢታንግ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ወረዳ በተወሰኑ ነዋሪዎች መካከል የተነሳ አለመግባባት በፍጥነት ብሔርን መሠረት ደዳደረገ ውጥረት መሸጋገሩን ከነዋሪዎች ሰምቻለሁ ብሏል ኢሰመኮ።
ከቀናት በፊት በክልሉ በአዲስ መልክ ግጭት ተቀስቅሶ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ ከሐምሌ 13/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ክልላዊ የሰዓት እላፊ መጣሉን አስታውቋል።
በሰዓት እላፊው መሠረት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተከልክሏል።
- አንድ ሚሊዮን ዶላር ቤታቸው ተገኝቷል የተባሉት የጋናዋ ሚኒስትር ሥልጣን ለቀቁከ 5 ሰአት በፊት
- ሩስያ ሞስኮ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ ስትል ዩክሬንን ወቀሰችከ 5 ሰአት በፊት
- ትዊተር አርማውን ከምናውቃት ወፍ ወደ ‘ኤክስ’ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ኢላን መስክ ገለጠከ 5 ሰአት በፊት
ኢሰመኮ በቅርቡ በተቀሰቀሰው ግጭት በተወሰኑ ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተባብሶ የተለያዩ ብሔር ታጠቂ ቡድኖች በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግ ወረዳ፣ እና በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ባሉ ሰፈሮች ጥቃት ፈጽመዋል።
በዚህም ሳቢያ በርካታ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት በክልሉ ውስጥ መድረሱን አመልክቶ፣ ችግሩ አሳሳቢ እንደሰሆነ የመብት ድርጅቱ ገልጿል።
በሰው እና በንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በፀጥታው ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በክልሉ ውስጥ የወደሙ መንገዶች መኖራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል ብሏል።
ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል ከጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን ድንበር ተሻግረው በሚገቡ ቡድኖች ጥቃቶች ከዚህ ቀደም እንደሚሰነዘሩ አስታውሶ፣ አሁን ላይ በክልሉ ወደ 350 ሺህ የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በስምንት የተለያዩ ካምፖች እንደሚገኙ ጨምሮ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሁን በክልሉ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ አፈጻጸም ነዋሪዎችን ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይዳርግ ጥንቃቄ እንዲደረግ፣ በክልሉ ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ጉዳት የዳረጉ ጥቃቶችን እና ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም ተጨማሪ ትኩረት እና ክትትል ማድረግ ይገባል ብሏል።
ባለፈው ዓመት የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በጋራ በጋምቤላ ከተማ ላይ ጥቃት በመክፈት ከተማዋ ለቀናት ከተለመደ እንቅስቃሴዋ ውጪ ሆና እንደቆየች እና ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።