ክትባት

ከ 4 ሰአት በፊት

የቡርኪና ፋሶ የጤና ባለስልጣናት አዲሱ የወባ ክትባት ለሕጻናት እንዲሰጥ ፍቃድ ሰጡ።

ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል መፈቀዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የወባ ወረርሽኝ ተጋላጮችን ሕይወት ይታደጋል የሚል ተስፋን አጭሯል።

አር12 የተሰኘው የወባ ወረርሽኝ ክትባት ከአሁን በፊት በሌሎች አገራት ይሁንታን አግኝቶ ጥቅም ላይ መዋል ጀምሯል።

ጋና እና ናይጄሪያ ለክትባቱ ፈቃድ የሰጡ ብቸኛ አገራት ናቸው።

ይህንን ክትባት ሰዎች እንዲወስዱት ፈቃድ በመስጠት ጋና የመጀመሪያዋ አገር ነች። ክትባቱን ያበለጸጉት ተመራማሪዎች ክትባቱ “ዓለምን የሚቀይር” ሲሉ ገልጸውታል።

በቡርኪና ፋሶ ለሕጻናትን ሞት ቀዳሚው ምክንያት የወባ በሽታ ነው። የአገሪቱ የጤና ሚንስትር ሮበርት ካርጉጉ ክትባቱ የሕጻናትን ሞት ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን የወባ ወረርሽኝን በአገሪቱ ለማጥፋትም ይጠቅማል ብለዋል።

በሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ መሪዎች እንዳይገኙ አሜሪካ እያደናቀፈች ነው ስትል ሞስኮ ወቀሰችከ 5 ሰአት በፊት

የጋና ፓርላማ የሞት ቅጣትን ለማስቀረት ድምጽ ሰጠከ 5 ሰአት በፊት

ልዩ ፍላጎት ላላት ልጃቸው ሲሉ ለዓመታት ዩኒቨርስቲ የቆዩት እናት እና በማዕረግ የተመረቀችው ልጃቸው25 ሀምሌ 2023

ወባ በዓመት 620 ሺህ ሰዎችን የሚገድል ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ ሕጻናት ናቸው። የመጀመሪያ ሙከራው እንደሚያሳየው አር12 የተሰኘው አዲሱ ክትባት ሦስት ጊዜ በመከተብ እስከ 80 በመቶ ድረስ ውጤታማ ነው።

ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ተጨማሪ ማጠናከሪያ አንድ ክትባት ይሰጣል። ከአገራት በተጨማሪ የዓለም ጤና ድርጅትም ክትባቱን ለማጽደቅ እየመረመረ መሆኑ ታውቋል።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት በ5 ሺህ ሕጻናት ላይ የተደረገው ሙከራ ውጤታማ ሆኗል።

ክትባቱ ከአምስት እስከ 36 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕጻናት ዝግጁ የሚሆን ሲሆን የክፍያው መጠንም ሁለት ዶላር አካባቢ ነው።

ሴረም ኢንሲቲቲዩት ኦፍ ኢንዲያ የተባለው ኩባንያ በዓመት 2 ሚሊዮን ክትባቶችን ማምረት ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ይኸው ኩባንያ ጋና ውስጥ ተጨማሪ ፋብሪካ ለመትከል እያሰበ ነው ተብሏል።