July 27, 2023 – Abebe Bersamo 

አብይ አህመድ በአማራ ብልጽግና ገጽ ላይ፣ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ መከላከያን አስመልክቶ ሶስት ተመሳሳይ መግለጫዎች እንዲወጣ አድርጓል፡፡ “መከላከያ ሠራዊታችን የሀገራችን የመጨረሻው ምሽግ እና የኢትዮጵያ የከፍታ ማማ ነው”፣ “ሁለገቡ የኢትዮጵያ ኩራት” እና “”የአማራ ህዝብ ትናንት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ደጀን ነበር ፤ ዛሬም አስተማማኝ ደጀን ሆኖ ይቀጥላል ” በሚሉ ርእሶች፡፡

ተመሳሳይ መግለጫዎች በተደጋጋሚ ለምን ማውጣት አስፈለ ? ብሎ መጠየቁ አስፈላጊ ነው፡፡ ዋልተር ላንገር የተባለ አሜሪካዊ የስነ አይምሮ ጠበብት፣ “ትልቅ ውሸት፣ ተደጋግሞ ከተነገረ እንደ እውነት ይቆጠራል፣ ( “If you tell a big enough lie and tell it frequently enough, it will be believed.) እንዳለው፣ ውሸትን ደጋግሞ በመጻፍና በመናገር በህዝቡ አይምሮ ለመጫወት ያሰቡ ይመስላል፡፡ ምን አልባትም ዙሪያቸው ያሉ የስነአይምሮ ባለሞያዎች የመከሯቸው ሊሆንም ይችላል፡፡

አንድ ውሸት ተደጋግሞ ሲነገር የሚዋሸው ሰው የለየለት ውሸታም መሆኑ ሰዎች ካወቁ፣ ሰምተው ንቀው ይተውታል እንጂ ስውዬው የተናገረውን እንደ እውነት የሚቀበል አይኖርም፡፡ የነ ዋልተር ላንገር አባባል የሚሰራው፣ የሚዋሸው ሰው ቢያንስ በህዝብ እንደ ውሸታም የማይቆጠር ከሆነ ነው፡፡

ለዚህም ነው ላለፉት 5 አመታት፣ ህዝብ፣ በዶር አብይ አህመድና በብልጽግናዎች ላይ ትንሽ ቢሆን እምነት ስለነበረው፣ ሲዋሹ፣ ሲሸረድዱ የነበረውን ነገር፣ እንደ እውነት ሲቀበል የነበረው፡፡ በመልካም ቃላቶች ህዝቡን ግራ ሲያጋቡትና ሲያወናብዱት ነበር፡፡ ባዶ ተስፋ እየሰጡት አጋንጦ እነርሱን ብቻ እንዲጠብቅ ሲያደርጉት ነበር፡፡

አሁን ግን ሁኔታ እጅግ በጣም ተቀይሯል፡፡ አብይ አህመድና ጨምሮ ጓዶቹ የለየላቸው ውሸታሞች (Certified liers) መሆናቸውን ህዝብ አውቋል፡፡ ንግግራቸው ገና ሳይጨርሱ ነው ምን ለማለት እንደፈለጉ የሚረዳው፡፡

” ፅንፈኛ ሀይሎች” የሚል ቃል በመጠቀም፣ እነ ማን እንደሆኑ በግልጽ ለመጥቀስ ያልፈለጉት ብልጽግናዎች፣ የመከላከያ ስም እየጠፋ ነው፣ መከላከያ ያልሆነውን ሆን እየተባለ ነው በሚል ነው በመግለጫዎቸው እየተንጫጩ ያሉት፡፡ “ፅንፈኛ ሀይሎች ሠራዊቱን በማጣጣል እና ስሙን ከምግባሩ ውጭ በማጠልሸት ከደጀኑ ህዝባችን(አማራው) ለመነጠል አጉል ተስፋ ሰንቀው ይድከሙ እንጂ መላው የአማራ ህዝብ እውነታውን በውል ይገነዘባል። ህዝባችን ማን መከታው እንደሆነ እና ለማን አስተማማኝ ደጀን እንደሚሆን ብሎም ማን ሰላሙን እያናው እና ልማቱን እያደናቀፈው እንደሆነም ይገነዘባል” ይላሉ፡፡

እነርሱ እንዲህ ይላሉ እንጂ ሜዳ ላይ፣ ህዝብ እያየ ያለው እውነታ ምንድንነው ? ብለን ብንጠይቅ በማስረጃ ብዙ፣ ራሱን መከላከያ ብሎ የሚጠራው ተቋም ለህዝብ የቆመ ሳይሆን በህዝብ ላይ የቆመ፣ ህዝብን የሚያገለግል፣ የሚጠበቅ የሚያድን ፣ ለህዝብ መከታ የሆነ ሳይሆን ህዝብን እያሸበረ፣ በህዝብ ላይ ጦርነት የከፈተ፣ ህዝቡን ለማፈን፣ ትጥቁን ለማስፈታት እየሰራና ከህዝብ ጋር እየተዋጋ ያለ ተቋም መሆኑን ነው የምንረዳው፡፡

አንዲት ብቻ ምሳሌ ላቅርብ፡፡ የሰሜን ምእራብ እዝ አዛዦች በባህር ዳር ስብሰባዎች አድርገው ነበር፡፡ ተራዉን ወታደር እያስፈጁ፣ እያስጨረሱ ፣ እነርሱ ግን በጎርጎራ ሪዞርቶች ለመዝናናት ወደዚያ ያመራሉ፡፡ ረእስ ሐምሌ 19 ቀን የአመቱ ገብርኤል ቀን ነው፡፡ በአካባቢው በትልቅ ሁኔታ የሚከበር፡፡ ጎርጎራ በርካታ ገዳማት ያሉባት እንደመሆኗ በዚያ ያለው ማህበረሰብ የኦርቶዶስክ እምነት ተከታይ፣ ኃይማኖተኛ ማህበረሰብ ነው፡፡

ከላይ እንዳልኩት ተራውን ወታደር በየቦታው እየላኩት፣ የሚበላውን ኮቾሮ እንኳን ማቅረብ አቅቷቸው ፣ ወታደሩን በረሃብ እያስፈጁት ያሉ የብልጽግና ጀነራሎች፣ ለነርሱ፣ በሚዝናኑበት ቦታ፣ በጎርጎራ፣ 11 በሬ ፣ በጾም ቀን ለማረድ ይነሳሉ፡፡ ፡የአካባቢው ሽማግሌዎች በጨዋ ደንብ ፣ የሰሜን ምእራብ እዛዦችን፣ “ድግሳችሁን ለምን ትላንት አላደረጋችሁት ነበር፣ ቢያንስ ነገ ሐሙስ አድርጉ” የሚል ጥያቄ አቀረቡላቸው፡፡ ጀነራሎቹ በንቀት ፣ ሰድበው አዋርደው መለሷቸው፡፡

ችግሩ በሬ ማረዱና አለማረዱ ላይ አልነበረም፡፡ “ዛሬ መመለስ አለብን፣ ለዚያ ነው፣ በጣም ይቅርታ” ብለው በጨዋነት ቢመልሱ ጥሩ ነበር፡፡ ግን ሰዎቹ ህዝብን የሚንቁ፣ ስነ ምግባር የሌላቸው እንጭጮች በመሆናቸው፣ የአካባዊን አባቶች አዋርደው ላኩ፡፡ ይህ የአካባቢዉን ህዝብ አስቆጣ፡፡ ተቃውሞ ተነሳ፡፡ በሰላም ተቃውሞ እያሰማ ያለው ማህበረሰብ ላይ መከላከያ ነን የሚሉ ተኮሱ፡፡ ስምንት ንጹሃን ዜጎችን ገደሉ፡፡

ይህን የሰሙ ፋኖዎች ህዝብን ማዳን አለብን በሚል መከላከያ ከሚባለው ጋር ገጠሙ፡፡ በጎርጎራ፣ ጯሂት እንዳለ በደምቢያ፣ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ኃይሎችና የአማራ ብልጽግናዎች ሕዝብን የሚጠብቅ ነው ባሉት ፣ ራሱን መከላከያ ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ተቀስቅሷል፡፡ ከጎርጎራ፣ በጫሂት፣ ቆላ ድባ አድርጎ ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል፡፡ በጎርጎራ ያሉ ጀነራሎች በየብስ መውጣት አልቻሉም፡፡ ምን አልባት ሄሊኮፕተር ከባህር ዳር ተልኮላቸው ወይንም በጀልባ ከግርጎራ ወደ ባህር ዳር ይሻገሩ ይሆናል፡፡

እንግዲህ እግዚአብሄር ያሳያችሁ ሰላም በነበረ አካባቢ ነው፣ የብልጽኛ ጦር ቀውስና ግጭት ጠማቂ ሆኖ በአካባቢው ሰላም እንዲደፈርስ ያደረገው፡፡

የጎርጎራውውን እንደ አንድ ምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ፣ በመላው የአማራ ክልል መከላከያ ከህዝብ ጋር ቢያንስ በ56 ከተሞች ውጊያ አድርጓል፣ ወይንም እያደረገ ነው፡፡

ከሁለት አመት በፊት መከላከያ የህዝብ ወዳጅ ነበር ተድርጎ የሚቆጠረው፡፡ አሁን እንደዚያ አይደለም፡፡ በፊት የመከላከያ አባላት በሄዱበት ህዝብ በነጻ ያጎርሳቸው ነበር፡፡ አሁን ገንዘብ ከፍለው ምግብ ቢጠይቁ የሚያቀርብላቸው የለም፡፡ ያንን ያህል ተጠልተዋል፡፡ በሰሜን ሸዋ በመርሃቤቴ ነው፡፡ ወደ አንድ ምግብ ቤት ይመጣል አንድ የመከላከያ አባል፡፡ “እንጀራ ፈልጌ ነው” ይላል፡፡ 5 ብር የሚሸጥን 50 ብር ይባላል፡፡ ለመከላከያ መሸጥ ስላልተፈለገ፡፡ “እሺ እከፍላለሁ” ብሎ 50 ብር ከኪሱ ሲያወጣ፣ “እንደውም አልቋል፣ የለንብም” ይሉታል፡፡ ያን ያህል ነው ህዝብ በመከላከያ ላይ እያመረረ ያለው፡፡ ለምን የመከላከያ ሰራዊት የአገር ሰራዊት ሳይሆን የአንድ ግለሰብ ፣ የአንድ ቡድን፣ ያውም የዘረኛ ኦነጋዊ ኦሮሙማ ቡድን ሰራዊት በመሆኑ፡፡

“ህዝባችን ማን መከታው እንደሆነ እና ለማን አስተማማኝ ደጀን እንደሚሆን ብሎም ማን ሰላሙን እያናው እና ልማቱን እያደናቀፈው እንደሆነም ይገነዘባል” ብለው የአማራ ብልጽግ ናዎች፡፡ አዎን ህዝብ ይውቃል፡፡ እነርሱ እንደሚዋሹት ለኦሮሙማ ገዢዎች የሚታዘዘውን መከላከያ ሳይሆን መከታዩእ የሚለው የአማራ ሓይሎችን ፋኖዎችን ነው፡፡ በጎርጎራ መከላከያ ህዝብን ሲገደል፣ ፋኖዎች ህዝብን ለማዳን ነበር የተሰለፉት፡፡

(በፋኖዎች በሰሜን ሸዋ ተማርከው ነው፡፡ ከሸዋሮቢት የተነሳ አንድ አይሱዚ ሙሉ የመከላከያ መኪና ወታዳር ከተጨማሪ ሁለት ፓትሮል ሙሉ ወታደር ጭኖ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራርን እና ሬሸን አጅቦ ወደ ደብረሲና እየሄደ እንዳለ ነበር፣ በፋኖዎች አስፋቸው ማፉዶ መታጠፊያ በሚባል ማዞሪያ ላይ በተሰራ የደፈጣ ኦፕሬሽን ፣ የታጀበው አመራር(ለጊዜው መአረጉ ኮሬኔል ይሁን ጀነራል በትክክል ያልተለየ) ሲገደል፣ 32 ሰራዊት ከነ ሙሉ ትጥቁ ሲማረክ ቀሪው በሙሉ ቁሰለኛ እና ሞት ተደርጎል። ከዚህ በታች ፣ ከተማረኩ መካከል፣ በጣም ሰልጥነዋል፣ ትልቅ ወታደራዊ ብቃት ያላቸው ናቸው፣ የሚባሉ ሬፓብሊካን ጋርድ፣ ኮማንዶ አባላት ናቸው፡፡ )