July 28, 2023 – Konjit Sitotaw
በአሁን ሰዓት ከተማዋ፡ በአማራ ህዝብ ሲነዛ የነበረውን የሀሰት ትርክት ስጋ አልብሶ ወደ ቤተመንግስት በማስገባት አማራን እንደ ኩርድ ህዝብ ለማጥፋት ሲንቀሳቀስ ከነበረው እራሱን ብልፅግና እያለ ከሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን ነፃ ሁናለች ተብሏል።
ፋኖን ትጥቅ እናስፈታለን በሚል ስም ነፍሰ ጡር እናቶችን ጨምሮ ህፃናት እና አዛውንቶች ላይ የከባድ መሣሪያ ውርጅብኝ በማውረድ የግፍ ጥግ ሲፈፅሙ የነበሩ ስርዓት የለሽ የአብይ አህመድ ወታደሮች በከተማዋ ደብዛቸው መጥፋቱንም የአማራ ድምፅ ነዋሪዎቹን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።
ከአማራ ጠሉ የብልፅግና ስርዓት ጋር ወግነው የገዛ ወገናቸው ላይ በመጠቆም ሲያስገድሉ፣ ሲያሳስሩና ሲያሳድዱ የነበሩ ሆድ አደር ካድሬዎች ከተማዋን ለቀው የሸሹ ሲሆን፡ ነገር ግን ነገ ከሚወድቅ ፓርቲ ይልቅ ዘመናትን የሚሻገር ህዝባችን ይበልጥብናል በሚል ከዚህ በፊትም ከህዝባቸው ጎን የነበሩ ውስን አመራሮች እና የፀጥታ አባሎች ፋኖ ወደ ከተማዋ ሲገባ በደስታ መፈንደቃቸውም ተሰምቷል።
የፋኖ አባላቱ ስምሪት በመስጠት በአሁን ሰዓት የከተማዋን ደህንነት እየጠበቁ ሲሆን በተጨማሪም ማህበረሰቡን ሰብስበው ማወያየታቸውን የአማራ ድምፅ ሚድያ ዘግቧል ።