July 28, 2023 

ነዓመን ዘለቀ ፡ ወደ ሀገር ቤት ሄዶ የተመለሰ እንድ ወዳጄ ከሸገር ከተማ ከተፈናቀሉት ውስጥ በግንባታ ላይ በሚገኙ ቤቶች በለቤቶቹ ፈቅደውላቸው ኩርምት ብለው አንዳገኛቸው፣ ጠጋ ብሎም ሲያናግራቸውም የደረሰባቸውን ግፍ እንደነገሩት፣ ስሜቱ በእጅጉ ተረብሾ እንደነበር አጫወተኝ። እንዲሁም በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ የተጫነው እዲስ ግብር በሚመለክትም፣ የእናትና አባቱ ገቢ ክፈሉ ከተባሉት የግብር መጠን ጋር ምንም የማይገናኝ ኢፍትህዊና ሌላ አጀንዳ እለው የሚል እምነት በህዝቡ ዘንድ በሰፊው እንደሚንጸባረቅ አጫወተኝ።

ከሰሞኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርና የዲያስፓራ ኤጀንሲ ሃላፊዎች በተለያዪ የአሜሪካ ግዛቶች፣ የካናዳና የአፍሪካ ሀገሮች በመጓዝ በዲያስፓራ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላትን ሲያወያዪ እንደነበር ይታወቃል። ከዳያስፓራው ጋር እየሻከረ የመጣውን ግንኙነት ለማስተካከል ጥረት ለማድረግ የታቀደ እንቅስቃሴ አካል ይመስላል። በአንዳንዶቹ አካባቢዎች ከተደረጉ የውይይት አጀንዳዎች መካከል በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገብተው ኢንቪሰት እንዲያደርጉ ማግባባት ኢላማ ያደረጉ ውይይቶችም ነበሩ። የአብዛኛው ኢትዮጵያውያን በውጭ የሚገኙና ሀገራቸው አብዝተው የሚወዱና ብዙ እስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩትን ጨምቶ ግልጽ ስጋጎች በብዙዎቹ ስብሰባዎች ተነስተዋል።

የህግ የበላይነት፣ ፍትህና ርእትእ፣ የህግና ስርአት መከበር (law and order)፣ የሰብአዊ መብቶች መከበር ጥያቄዎች ተነስተዋል። የዜጎች ደህነንትና የመኖር ዋስትና፣ ዜጎች በማንነታቸው/በብሄራቸው ተነጥለው ለእንግልት፣ ለመፈናቀል ፣ በህገ ወጥ ግንባታ ስም ከ 110,000 በላይ ቤቶች ማፍረስና ፣ ቢያስን ከ500,000 የሚገመቱ ያ ሰው መሳይ አውሬ የሸገር ከንቲባ “ህጋዊ ድሃ አደረግናቸው” በማለት የተሳለቀባቸው ወኖቻችን ለመከራና ለስቃይ፣ ለሞትም ጭምር ያዳረግ እጅግ ነውረኛ፣ ልብ የሚደማ ጭካኔ ያጢኑአል። ለእስራት፣ ለግዳያ፣ ለመከራ፣ በጨለማ ቤቶች ለሰቆቃ የሚዳረጉበት፣ ጠ/ሚ በአንድ ወቅት ያለፈው አስከፊ ስርአት መገለጫ የሆነው ማእከላዊን ዘግተናል ብሎ ካወጀ በኋላ የኦሮሚያ ብልጽግና ደህነቶችና ካድሬዎች በገላንና በአዲስ አበባ ፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ የሚደረጉት አፍኖ ሰቆቃ መፈጸም ለማሳያ ማንሳት ይቻላል።

ከአዲስ አባባ 50-100 ኪ ሜ ርቀት መንቀሳቀስ የማቻልበት፣ በተደጋጋሚ ዜጎች የሚታፈኑበት፣ በመቶ ሺዎችና በሚሊዮኖች በየግዜው “በኦነግ ሸኔ” ስም በሚፈጸሙ እነዚህንና ሌሎች ወንጀሎችን መቆጣጠር ያልተቻለበት ሀገራዊ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን። ሌሎችም በርካታ ማሳያዎችና ክስተቶች እንደሚያረጋግጡት መንግስትን ላይ ነፍጥ ባነሱ እንደ ኦነግ ሸኔ አይነት ሃይሎች ብቻ ሳይሆን በመንግስታዊ ሃይሎች፣ እንዳንዴም በራሱ በጠ/ሚንስትሩ እና በኦሮሚያ ብልጽግና መሪ ካድሬዎች ትእዛዝና እውቅና የሚፈጸሙ ጥቃቶችና አፈናዎች ሳቢያ መሆኑ በተደጋጋሚ ተረጋግጦአል ( በዜጎች ላይ የሚደርሱ የሰበአዊ መብቶች ረገጣና አፈና በሚመልከት ለምሳሴ በኢሰመጉ፣ ኢሰመኮ፣ ቪኦኤ በየገዜው የተዘገቡ ያጢኑዋል)።

እንዲያውም እነዚህ ዝርዝሮች አገራችን በበርካታ መለኪያዎች -ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ የደህነነት፣ ወዘተ የምትገኝበት ጥልቅ የሆኑ በርክታ ስጋቶችና አደጋዎች ያንዣበቡበት፣ እስከፊ፣ አሳፋሪና አሳዛኝ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ አይገልጽም። ስለሆነም በዛሬዋ ኢትዮጵያ መንግስትን መንግስት የሚያደርጉትን ከላይ የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ተግባራት ማረጋገጥ ባልቻለበት (በማይፈልግበት ሁኔታ) ፣ ዜጎች በሙሉ እምነት ሀገራቸው ላይ ኢንቪሰት ለማድረግ ሊታሰብ አይችልም።

እነዚህ ሃላፊዎችና የልኡካን ቡድን አባላት እንዳንዶቹ መልካም ሰዎች ቢሆኑም ቅሉ ፣ የችግሮቹ ቁልፍ ግን የሚገኘው፣ በመሰለው ፣ በዘፈቀደና ፣ በእውር ድንብር ውሳኔዎችና እርምጃዎች እየወሰደ፣ የዛሬ አምስት አመት ወደ ስልጣን ሲመጣ ቃል የገባውን አጥፎ፣ ህዝብን በእኩልነት ማስተዳደር፣ መብቶቹን ክብሩን ጥበቆ በእኩል አይን ለማየት የተሳነው፣ በራሱ ቅዠት አለም የሚኖር፣ ማንንም የማይሰማ፣ ራሱን ብቻ የሚሰማ መሪ ዛሬ ላይ ሀገራችን ለምትገኝበት በርክታና ተደራራቢ፣ ችግሮች እንዲያውም እየተጣፉ/ኮምፓውንድ እየሆኑ የመጡ ቀውሶች ዋና እምብርትና ተጠያቂ በመሆኑ ነው። በተጠሩት ስብሰባዎች ላይም የተገኙ አንዳንድ ጠንካራ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ያነሱዋቸው ጥያቄዎች ይህን ሃቅ አንጸባርቀዋል።

ወደ አምባገነናዊ አገዛዝ የተቀየረው የአብይ አገዛዝ ውድቀቱን ከማፋጠኑ በፊት ፣ ራሱንና ህዝብን ከማታለል፣ የሌውን አለ፣ የላሆነውን ሆነ፣ በማለት በየእለቱ የራሱን ሃስቶች እያመነ፣ ጸረ ህዝብና ጸረ ደሃ ተግባሮቹን በመግታት መራራ ቢሆንም የሀገሪቱን እስከፊ ሁኔታ መገምገምና መንገዱን ማስተካከል ከቻለ ሊድን ይችል ይሆናል። የመሪዎች የልቦና ውቅር የደነደነ፣ በቅዥት እለም የታጀለ ፣ ፈረንጆቹ እንደሚሉት ዲሉሽናል/delusional በመሆኑ የሚሆን እይመስልም። ነዓመን ዘለቀ