
ከ 5 ሰአት በፊት
የተለያዩ የዓለም ክፍሎችን በከፍተኛ ሙቀት እያቃጠለ ያለው ያለንበት ወር ሐምሌ በዓለም ታሪክ በከፍተኛ ሁኔታ ሞቃት ተብሎ የሚመዘገብ እንደሆነ ሳይንቲስቶች ገለጹ።
የሐምሌ ወር ሊጠናቀቅ ቀናት እየቀሩት አስካሁን የተመዘገበው የሙቀት መጠን ከአራት ዓመታት በፊት በ2019 (እአአ) ከፍተኛ ተብሎ የተመዘገበውን የሙቀት መጠን ይበልጠዋል ተብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንዳሉት ምድራችን “ወደ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ዘመን እየገባች ነው” ሲሉ ሁኔታውን ገልጸውታል።
ሳይንቲስቶች እንደሚስማሙት አሁን ለተከሰተው ከፍተኛ መቀት በዋነኝነት በዓለም ላይ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ነዳጅ ዘይት ምክንያት ነው።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዓለም ላይ እየታየ ያለው የአየር ፀባይ ለውጥ የሰው ልጅ “ህልውና ስጋት ነው” በማለት፣ ከዚህ በኋላ “የአየር ፀባይ ለውጥ መኖሩን ማንም ሊክድ አይችልም” ብለዋል።
- ሁለት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የደም ግፊትን እንደሚቀንሱ አንድ ጥናት አመለከተ27 ሀምሌ 2023
- በአሜሪካ ሙቀት ምክንያት ተቃጥለው ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ጨመረ25 ሀምሌ 2023
- በአውሮፓ እና በአሜሪካ አገራት የተከሰተው ከባድ የሙቀት ማዕበል እና ኢትዮጵያውያን18 ሀምሌ 2023
አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉት በዚህ ዓመት ሐምሌ ወር ያጋጠመው ከፍተኛ ሙቀት ባለፉት 120,000 ዓመታት በሐምሌ ወራት ውስጥ ከተመዘገቡት ሁሉ የላቀ ሳይሆን አይቀርም ብለዋል።
ባለንበት የሐምሌ ወር በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወስጥ እያጋጠመ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ተመራማሪዎች በክስተቱ እምዛም አልተደነቁም።
በዓለም ታሪክ ሞቃቱ የተባለው ዕለት በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 06/2023 ሲሆን፣ ያለፉት 23 ቀናት ደግሞ ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበባቸው መሆናቸውን ኮፐርኒከስ የተባለው የአየር ፀባይ ለውጥ ክትትል ተቋም አመልክቷል።
ተመራማሪዎች እንደሚሉት በአሁኑ ጊዜ እየተከሰተ ላለው ከባድ ሙቀት፣ የሰው ልጅ አገልግሎት ላይ ከሚያውለው የነዳጅ ዘይት የሚወጣው በካይ ጋዝ ጉልህ ሚና አለው።
ባለሙያዎች እንደሚሉት ባለንበት የሐምሌ ወር የተከሰተው የምድራችን ከፍተኛው የሙቀት መጠን የመጨረሻው እንደማይሆን በመግለጽ፣ የበካይ ጋዞች ልቀትን መቆጣጠር ካልተቻለ የሙቀት መጠኑ ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል አመልክተዋል።
በተጨማሪም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ላይ የሚከሰቱ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች የምድርን የአየር ፀባይ ለውጥ እያፋጠኑት መሆናቸውንም ባለሙያዎች ይናገራሉ።