July 29, 2023 – BBC Amharic 

የዩክሬን የኦርቶዶክስ በዓል አከባበር

ከ 8 ሰአት በፊት

ዩክሬን የገና በዓል መላው ሩሲያን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ከሚያከብሩበት ታህሳስ 29 ወደ ታህሳስ 16 ወይም ወደ ጎሮጎሳውያኑ ታህሳስ 25 እንዲዛወር ወሰነች።

ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ “ ከሩስያ የተወረሰውን የገና በዓል አከባበር ትውፊት” ለማስወገድ ያለመ የፓርላማ ህግን ፈርመዋል።

ዩክሬን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሩሲያ ጋር ያላትን ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ሌሎች ግንኙነቶችን በመቁረጥ ከምዕራቡ ዓለም ጋር አጋርነትን መርጣለች።

በተለይም ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራም ተከትሎ የበለጠ እንዲፈራቀቁ አድርጓቸዋል።

የገናን በዓል የሚቀይረው ይህ ህግ ከጸደቀ ከሁለት ሳምንታት በኋላም ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ አርብ ዕለት ፈርመውበታል።

ህጉ በተጨማሪም ሌላ ሁለት የመንግሥት በዓላትንም ቀን አዛውሯል። የዩክሬን የአገር ምስረታ የተባለው ክብረ በዓልን ከጎሮጎሳውያኑ ሐምሌ 28 ወደ ሐምሌ 15 እንዲሁም የቀድሞ የጦር ዘማቾች የሚከበሩበት ዕለትም ከጥቅምት 14 ወደ ጥቅምት 1 እንዲዛወር መደረጉም ተገልጿል።

ሩሲያ እስካሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠችም።

ዩክሬንን ጨምሮ የአገራት ጥምረት የነበረችውን ሶቪየት ኅብረት ለዘመናት በዋነኝነት በሩሲያ ትመራ የነበረ ሲሆን ዩክሬንን ከኅብረቱ መውጣቱ በፊትም ቢሆን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አልተቻለም።

ሲደረግ ከነበረው ቁጥጥርም መካከል የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በዩክሬን አብያተ ክርስቲያናት ላይ የነበረው ጫና ነው።

ሆኖም በጎሮጎሳውያኑ 2019 በቅርቡ የተመሰረተችው የዪክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአለም ዙሪያ ባሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ መሪ ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ ነጻነቷን አግኝታለች።

ይህ ውሳኔ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬንን ወረራ በግልጽ የሚደግፉት በሩሲያው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ቁጣን አስነስቷል።

የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሩሲያን ጨምሮ እንደ ሌሎች በርካታ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጁሊያን የቀን አቆጣጠር መሰረት የገና በዓልን የሚያከብሩት ታህሳስ 29 ዕለት ነበር። ነገር ግን በዘንድሮው ዩክሬን በአብዛኛዎቹ የዓለም ክፍሎች ወደሚገለገልበት የጎሮጎሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ታከብራለች።ምናልባትም ሁለት ጊዜም ሊያከብሩ የሚችሉም ይኖራሉ።