
ከ 8 ሰአት በፊት
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በትዊተር ገጹ መሪያቸው ተዋጊዎቻቸውን ሲያነቃቁ የሚያሳይ ቪዲዮ አጋርቷል። ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ መሪው በቪዲዮ ሲታዩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።
ሄሜቲ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ጀኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ሰውነታቸው ከስቶ የታዩ ሲሆን አንዳንዶች እንደሚሉት ደግሞ እጃቸውን ባልተለመደ ሁኔታ ይዘዋል ይላሉ።
በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ሄምቲ በጦርነቱ ተጎድተዋል የሚል ወሬ በስፋት ይናፈስባቸው ነበር።
በንግግራቸው ሄሜቲ የተለመደ ትችታቸውን አቅርበዋል።
ትችታቸውም በቀድሞ አለቃቸው እና አሁን በብርቱ በሚፋለሟቸው የሱዳን ጦር አዛዥ ጀኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ላይ ያነጣጠረ ነው።
በንግግራቸው የሱዳን የጦር አመራር የሚቀየር ከሆነ በ72 ሰዓታት ውስጥ ለሰላም እጃቸውን እንደሚዘረጉ አስታውቀዋል።
- ዩክሬን ከሩሲያ ትውፊቶች ራሷን ለማራቅ የገና በዓልን ዕለት ቀየረችከ 8 ሰአት በፊት
- የኒጀር መፈንቅለ መንግሥት መሪ እና የፕሬዝደንቱ የክብር ዘብ አዛዥ ጄኔራል ቺያኒ ማን ናቸው?28 ሀምሌ 2023
- ሩሲያ የዩክሬንን እህል የመላክ ስምምነት እንድታከብር የግብጹ መሪ አሳሰቡከ 9 ሰአት በፊት
ሄሜቲ ወደዚህ ማዕረግ የደረሱት ከጃንጀዊድ ሚሊሻ ተነስተው ነው። ይህ የጃንጀዊድ ሚሊሻ በዳርፉር የዘር ፍጅት በመፈጸም ይከሰሳል።
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የተቋቋመው በ2019 ከስልጣን በተወገዱት በኦማር አል በሽር ነበር።
ይሁን እንጅ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ኦማር አልበሽርን ከስልጣን በማስወገዱ ረገድ የራሱን ድጋፍ አድርጓል። በሂደትም ከፍተኛ ስልጣን እናገኛለን የሚል ተስፋ ነበራቸው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አባላት።
ነገር ግን ሄሜቲ ከጀኔራል አልቡርሃን ጋር የነበራቸው አጋርነት ከሦስት ወር በፊት ወደ ከፋ ሁኔታ አምርቶ አፈ ሙዝ ተማዘዋል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ታላቋን ካርቱም ወደመሰረቱት ሦስት የመኖሪያ ከተሞች ተሰማርተዋል። እነዚህም ባህሪ፣ ካርቱም እና ኦምዱርማን ሲሆኑ ከፍተኛ የአየር ድብደባ ደርሶባቸዋል።
ሄሜቲ በንግግራቸው በዋናነት አጥብቀው የተቹት ያሲር አል-አታን ነው። ያሲር አል- አታ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ሲሆኑ ኦምዱርማን ውስጥ ያለውን ዘመቻ የሚመሩ ናቸው።
ሄሜቲ ጦርነቱ ለፈጠረው ቀውስ የሱዳንን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጦርነቱም ያለፍላጎታቸው በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ላይ የተቃጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለአምስት ደቂቃ በቆየው ንግግራቸው በበርካታ ወታደሮች ታጅበው ታይተዋል። ሰራዊታቸው በካርቱም እና ሌሎች አካባቢዎች ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽሟል መባሉንም አስተባብለዋል።