በሀንጋሪ ቡዳፔስት የአትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው ቡድን አባል የኾነው አትሌት ጥላሁን ኀይሌ፣ በአምስት ሺሕ ሜትር ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶችን አስመልክቶ የተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ በማኅበራዊ የመገናኛ ትስስሮች ቅሬታውን አሰምቷል።
በውድድሩ ለመሳተፍ የሚያበቃውን ሰዓት እና የአካል ብቃት አሟልቶ ወደ ውድድሩ ስፍራ ከመጣ በኋላ፣ በእርሱ ምትክ አትሌት በሪሁ አረጋዊ እን…
