September 5, 2023 – DW Amharic 

የወጣቱ ሥጋትና ሽሽት

ወጣት ነዉ።የባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪ።ባለፈዉ ግንቦት ማብቂያ ለዕረፍት ወደ ትዉልድ ከተማዉ ሔደ-ፈረስ ቤት፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ፣ ምዕራብ ጎጃም።ደዉልኩለት፤ ሥልኩን አነሳዉ። ከሱ ድምፅ በፊት ጫጫታና ጩኸት ብጤ ከጆሮዩ ገባ።«ትሰማኛለሕ?« አልመለሰልኝም።«ኸወዲያ ነዉ! አዎ!» እያለ ይናገራል ጮክ ብሎ።ያለኸልሐልም። እንደገና ጠየቁት «ይሰማል?» አዎ ቀጥል—ይቅርታ እየተኮሱብን ሆኖ ነዉ»
«ማነዉ ተኳሹ? የትናችሁ?» አከታትዬ ጠየቅሁት።«ፈረስ ቤት አካባቢ ነን።መከላከያ እየተኮሰብን ነዉ»
«ፈረስ ቤት ከተማ ዉስጥ ናችሁ? እናንተ አካባቢ ግጭት አለ ይባላል?» እንደገና ጠየቅሁት።
«ፈረስ ቤት አካባቢ በጣም የገነነ ችግር አለ።ከተጀመረ 3 ወር ምናምን ሆኖታል።የተወሰነ ጊዜ አርፈን ነበረ።በወራቸዉ መጥቶ መከላከያ ተኩስ ጀመረ።በጣም በጣም የሚያስጠላ ነገር ነዉ።በከባድ መሳሪያ ነዉ የሚጨፈጨፈዉ ንፁሐን—ሕፃናት አሉ።ነብሰ-ጡሮች አሉ።»
ጥቃትና ስጋት-ደጋ ዳሞት

እሱ እንደሚለዉ እሱና የቅርብ ሰዎቹ ፈረስ ቤት ከተማን ጥለዉ በግምት 3 ኪሎ ሜትር ወደሚርቅ ጫካ ከገቡ ሳምንት አልፏቸዋል።ዛሬ እነሱ የተሸሸጉበት አካባቢም ይተኮስበት ጀመር።የደወልኩለት እሱና አብረዉት ያሉት ሰዎች የተሻለ ከለላ «ምሽግ» ይለዋል እሱ ፍለጋ ሲጣደፉ ነዉ።ከተማ ዉስጥ (ፈረስ ቤት) ዉጊያ የለም። አካባቢዉና በየመስመሩ ግን ዉጊያ እየተደረገ ነዉ-ወጣቱ እንዳለዉ።»
«ፋኖ አይተን አናዉቅም፤ ጓደኞቼ ሙተዉብኛል»

«ከተማ ዉስጥና ባካባቢዉ ፋኖዎች መሽገዋል ማለት ነዉ?» ጥየቅሁት።
«አዎ!! ፋኖ ይላሉ ግን እኛ አይተናቸዉ አናዉቅም።»
«የሚዋጋዉ ታዲያ ማነዉ?
«ፋኖ ይላሉ፤ ግን አጠቃላይ ሕዝቡ በከባድ መሳሪያ፣ በዲሽቃ፣ በዙ 23፣በታንክ—-ነዉ» እየተደበደበ ያለዉ።
«የተጎዳ ሰዉ አጋጥሞሐል ወይስ ቀድመሕ ነሕ ነዉ የሸሸኸዉ።» ጠየቅሁት።መለሰም «እንዴ!! እንዴ—-ኧረ!» እያለ።«በኛ ዙሪያ አካባቢ እንኳን እንደዚሕ ብሎ ለመናገር ባይቻልም ማለት ነዉ፣እኔ ብቻ ቢያንስ ከ100 በላይ ሰዎች አዉቃለሁ።ቁስለኛ ከ50 በላይ።የኔ ጓደኞች ከአስራ ምናምን በላይ ሙተዉብኛል።»
አሁንም እየተጓዝክ ነዉ? ትንፋሽሕ/—-»አላስጨረሰኝም።
«አዎ ከባድ መሳሪያ እየተወረወረብን ነዉ።ምሽግ እየያዝን ነዉ እየሮጥን።»
ለሌላ ጊዜ ተቀጣጠርን።ካገኘሁት።
( የጀርመን ድምፅ ራዲዮ )