September 20, 2023 – VOA Amharic
በኩፍኝ፣ ተቅማጥ፣ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እና በሌሎችም መከላከል በሚቻሉ ሕመሞች ሳቢያ፣ ግጭት ከ5 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባፈናቀለባት ሱዳን፣ በየወሩ አንድ መቶ የሚሆኑ ሕጻናት ይሞታሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ካለፈው ግንቦት እስከያዝነው መስከረም ወር ድረስ ባለው ግዜ ውስጥ፣ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 1 ሺሕ 200 ሕጻናት በኩፍኝ ወረርሽኝ እና በተመጣጠነ ምግብ ዕ…
