
ከ 7 ሰአት በፊት
የኮሮና ቫይረስ ለረጅም ጊዜ ጠንቶባቸው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች በወሳኝ የሰውነት ክፍላቸው ላይ ጉዳት ሊኖር እንደሚችል አዲስ ጥናት አመላከተ።
በኮቪድ ለረጅም ጊዜ ተይዘው የነበሩ ሰዎች ሳምባ፣ አእምሮና ኩላሊት ከሌሎች ሰዎች በሶስት እጥፍ ከፍ ችግር እንደገጠማቸው የኤም አር አይ ምርመራ ፍንጭ ሰጥቷል።
ተመራማሪዎቹ ይህ ጉዳት በኮቪድ 19 በተያዙበት ወቅት በሽታው ምን ያህል የከፋ ነው ከሚለው ጋር የሚገናኝ ነው።
ይህ ጥናት በዩኬ እየተደረገ ያለውን በኮሮና ቫይረስ ለረጅም ጊዜ የተያዙ ሰዎች እየተዘጋጀ ያለውን ህክምና ውጤታማ ለማድረግ እንደሚረዳ ታምኖበታል።
ጥናቱ በኮቪድ 19 ተይዘው ሆስፒታል የገቡ 259 ሰዎችን ተሳታፊ አድርጓል።
ታካሚዎች ከ 5 ወራት የሆስፒታል ቆይታ በተደረገላቸው የኤም አር አይ ምርመራ ወሳኝ የውስጥ ሰውነት ክፍላቸው ፈጽሞ በኮቪድ ካልተያዙ 52 ሰዎች ጋር ሲነጻጸር ልዩነት አሳይቷል።
ጉዳቱ ይበልጥ ጎልቶ የታየው ሳምባ ላይ ሲሆን የኤም አር አይ ምርመራው ከሌሎች ሰዎች በ14 እጥፍ ከፍ ያለ የተለየ ሁኔታን አመላክቷል።
ምርመራው በኮሮና ቫይረስ ለረጅም ጊዜ የተያዙ ሰዎች አእምሮው ላይ ሶስት እጥፍ ኩላሊት ላይ ደግሞ ሁለት እጥፍ ከሌሎች የተለየ የጤንነት ሁኔታን አሳይቷል።
ሆኖም በልብና ጉበት ላይ የጎላ ልዩነት እንደሌለ ጥናቱ አይቷል።
- ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአሜሪካ ጥብቅ መረጃዎችን ለኢትዮጵያ አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ22 መስከረም 2023
- አንጋፋው የአሜሪካ የምክር ቤት አባል የግብጽን መንግሥት ለመደገፍ ጉቦ ተቀብለዋል የሚል ክስ ቀረበባቸውከ 8 ሰአት በፊት
- በባህር ዳር ሊካሄድ የነበረው ዓመታዊው የጣና ፎረም ተራዘመ22 መስከረም 2023
ይህንን ጥናት በመሪነት ከሚያካሂዱት መካከል አንዷና የኦክስፎርድ ባልደረባ ዶክተር ቤቲ ራማን ለረጅም ጊዜ ኮሮና ቫይረስ የጠናባቸው ሰዎች ከሌሎች ከፍ ያለ የሰውነት ክፍል ጉዳት ሊገጥማቸው እንደሚችል ግልጽ ነው ብለዋል።
ይህ ምርምር በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች የሚደርስባቸውን የረጅም ጊዜ የጤና ተጽዕኖንን ለማወቅ የሚደረግ ሰፊ የጥናት አካል ነው።
ተመራማሪዎቹ ምርመራ ወቅት የሰውነት አካል ጉዳት ምልክቶች ለረጅም ጊዜ በኮሮና በተያዙ ሰዎች ላይ መታየቱን ገልጸዋል።
ሆኖም ሁሉም ምልክቶች በኮሮና ቫይረስ ለረጅም ጊዜ በመያዝ ብቻ የሚመጣ ላይሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።
