

· ከአዲስ አበባ ማኅበራዊ ንቅናቄ (አማን) የተሰጠ መግለጫ
የአዲስ አበባ ሕዝብ ሁሉንም አሜን ብሎ በመቀበሉ በጎጥ መቧደን አለመቻሉ ዘመን ባገነናቸው ገዢዎች እንደ ኃጢአት ተቆጥሮበት ግፍና መከራን እየተቀበለ ይገኛል።
ይህ ትግል ህልውናችንን ለማስጠበቅ የሚደረግ ትግል ነው።
ይህ ትግል በሕይወት ለመቆየት የሚደረግ ትግል ነው።
ይህ ትግል የአዲስ አበባን ሕዝብ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መብት ለማስጠበቅ የሚደረግ ትግል ነው።
ይህ ትግል ነጋችንን የምንወስንበት ትግል ነው።ይህ ትግል ቀጣይ እጣ ፋንታችንን ለመወስን የተረጋገጠ ሰላምን ለማምጣት የሚደረግ ትግል ነው።
ይሄን ትግል ከግብ የምናደርሰው ብልፅግና በሚሰጠን ተስፋ ሳይሆን በተባበረ ክንዳችን ብቻ ነው፡፡
መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ እና ኢትዮጵያውያን ሁላችሁም ይህን ንቅናቄ እንድትቀላቀሉና እንድታግዙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
