September 25, 2023 – ተስፋዬ ወልደስላሴ 

የባህር ዳር ፋኖ ሌሊቱን በተጠና ደፈጣ ሶስት ፓትሮል ሙሉ ኮማንዶ ደመሠሠ

ትናንት ባህር ዳር ዙሪያ ተንታ ቂርቆስ ላይ ነፍሰ ገዳዩ ኮማንዶ ቡድን ንጹሀን አሳ አስጋሪዎችን ጨፍጭፎ ነበር ።

ያም ሆኖ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ካሉት በርካታ ክንፎች አንደኛው ዛሬ ሌሊት 9:00 አካባቢ አዴት መውጫ የአድማ ብተና ካምፕ ፊት ለፊት አፍንጫቸው ስር አጸፋዊ የደፈጣ ኦኘሬሸን ፈጽሞ ሶስት ፓትሮል ሙሉ ኮማንዶ ጭቃ አድርገውታል ።

የደም መላሹ ፋኖ አመራሮች እንደገለጹት ከሆነ ባህር ዳር አካባቢ በፓትሮል የሚንቀሳቀሱ ኮማንዶዎች ላይ በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ  በተከታታይ ጥቃቶች ለመፈጸም ዝግጅቱን ስለጨረሰ የባህር ዳር ነዋሪ ከወዲሁ ራሱን ወራሪው ኮማንዶ ከሚንቀሳቀስበት ቦታ በመራቅ የጥቃቱ ሰለባ እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል !!