
25 መስከረም 2023, 13:47 EAT
በለንደን የሚገኙ ፖሊሶች የጦር መሳሪያ ትጥቃቸውን ማስረከባቸውን ተከትሎ የአገሪቱ መከላከያ ድጋፍ እንዲሰጡ ወታደሮችን ለማሰማራት ጠየቀ።
ከአንድ ወጣት ግድያም ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ፖሊሶች የጦር መሳሪያ መያዝ የሚያስላቸውን ፍቃድ እንዲመልሱ መደረጋቸውንም አንድ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በለንደን ከ2ሺህ 500 በላይ የታጠቁ ፖሊሶች አሉ።
ይህ እርምጃ እየተወሰደ ያለው የጦር መሳሪያ ያልታጠቀ አንድ ግለሰብ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ነው።
በለንደን ፖሊሶች የተገደለው ግለሰብ ዕድሜው 24 ዓመት ሲሆን ክሪስ ካባ ይሰኛል።
የለንደን ፖሊስ ዋና ኃላፊ ሰር ማርክ ሮውሊ የሃገር ውስጥ ጽሕፈት ቤት በታጠቁ ፖሊሶች ላይ ያደረገውን ግምገማ በበጎ እንደሚቀበሉት አስታውቀዋል።
ለሃገር ውስጥ ጽህፈት በጻፉት ደብዳቤ ፖሊሶቹ በዚህ ደረጃ መያዛቸው ትክክል እንደሆነ ቢያምኑም ነገር ግን አሁን ያለው አሰራር የፖሊስ አባላቶቹ ላይ ተፅእኖ እያደረሰ ነው ። ተጨማሪ የህግ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።
ክሪስ ካባን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር።
አንዳንድ የፖሊስ አባላትም አቃቤ ህግ በፖሊሱ ላይ ክስ ለመመስረት መወሰኑ “በእነሱ ላይ ስለሚያሳድረው ተፅእኖ” ስጋት ገብቷቸው እንደነበር ሜት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
- በአዲስ አበባ ሲደረግ የነበረው የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ያለምንም ውጤት መጠናቀቁ ተነገረ25 መስከረም 2023
- በጎንደር በነበረ ግጭት ከ50 በላይ ‘የፋኖ ታጣቂዎች’ መገደላቸውን መከላከያ አስታወቀ25 መስከረም 2023
- በኦርቶዶክስ ገዳም ውስጥ ከተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ኮሶቮና ሰርቢያ ተፋጠጡ25 መስከረም 2023
ከጥቂት ወራት በፊት የጦር መሳሪያ ትጥቁን የፈታ አንድ የቀድሞ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ የተጋረጠው አደጋም “በጣም ከፍተኛ” ነው ሲልም ለቢቢሲ ተናግሯል።
ስሜ አይጠቀስ ያለው ፖሊስ “ለእኔ ግልጽ የሆነው ጉዳይ ፖሊሶች በንዴትም ሆነ በደም ፍላት የሚሰሩ አይደሉም”
“እነዚህ የፖሊስ አባላት የትዳር አጋሮች እና ቤተሰቦች ያሏቸው ናቸው። ለሙያቸውም ቁርጠኛ ናቸው” ብሏል
የመከላከያ ኃይል ወታደሮች ፖሊሶችን በስራ ለማገዝ ከተገደዱ “በጣም አሳዛኝ ቀን ነው” ሲልም ተናግሯል።
ባለፈው ዓመት መስከረም ላይ መኪና እየነዳ በነበረበት ወቅት ነበር ክሪስ ካባ በፖሊስ በጥይት የተመታው።
አባት ለመሆን ወራቶች ብቻ ቀርተውት የነበረው ክሪስ በማግስቱ በሆስፒታል ህይወቱ አለፈ።
የግንባታ ሰራተኛው ንብረትነቱ የሱ ያልሆነ መኪና እያሽከረከረ ነው የተገደለው።
ሞቱም በርካታ ተቃውሞዎችን አስከትሏል።
